የልብና የደም ቧንቧ ጤንነትዎን በልብ ካቴተራይዜሽን (Cardiac Catheterization) ያረጋግጡ - Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand.

የጤና መረጃዎች

የልብና የደም ቧንቧ ጤንነትዎን በልብ ካቴተራይዜሽን (Cardiac Catheterization) ያረጋግጡ

Share:

የልብ ካቴተራይዜሽን (Cardiac Catheterization) ዶክተሮች የልብዎን እና የደም ቧንቧ ስርዓትዎን ጤንነት ለመመርመር የሚረዳቸው እጅግ ውጤታማ የሆነ ዘዴ ነው፡፡ታካሚው ሳይተኛ(ነቅቶ) ነገር ግን በደንብ እንዲረጋጋ በማድረግ የሚከናወን ሰውነትን መቅደድ ሳያስፈልግ (minimally-invasive) የሚከናወን የምርመራ ሂደት ነማወቅ ያገለግላል፡፡ እንዲሁም የልብ እና የደም ቧንቧ ችግሮችን ለማስተካከል በሚደረጉ ህክምናወች ላይ የህክምው።

ለልብ ህመም አጠራጣሪ የሆኑ ምልክቶች እንዳሏቸው ለሚናገሩ ህመምተኞች ይህ የምርመራ ዘዴ ችግሩ ምን እንደሆነ ለናው አካል በመሆን አገልግሎት ላይ ይውላል፡፡

የልብ ካቴተራይዜሽን (Cardiac Catheterization) ምን ይነግረናል?

የህክምና ቅደም ተከተሉ በክንድዎ ወይም ከብልታችን አካባቢ በሚገኝ ዋና የደም ሥር (ቬይን ወይም አርተሪ) ውስጥ የሚገባ ረዥም ቀጭን ካቴተር ይጠቀማል፡፡ ከዚያም ካቴተሩ ወደ ልብ እስኪደርስ ድረስ በደም ሥር ውስጥ እንዲሄድ ይደረጋል፡፡

እንደ ህክምናው ዓላማ የተለያዩ ዓይነት ካቴተሮች እንጠቀማለን፡፡ ወደ ኮምፒውተር ስክሪኑ በሰአቱ ያለውን ሁኔታ የሚያሳዩ ምስሎችን ለመቅረጽ ለመላክ ፋይበር ኦፕቲክ መብራቶች እና ትንንሽ ካሜራዎች አሉት፡፡ አንዳንዶቹ የጠበበ የደም ቧንቧን ለማስፋት የሚያገለግሉ ፊኛዎችን ወይም ተጣጣፊ ቱቦዎች (stents) አላቸው፡፡

በዋናነት ለታካሚው የሚደረጉ ዝግጅቶች በሁሉም የልብ ካቴተራይዜሽን ሂደት ላይ አንድ ዓይነት ነው፡፡ ከሂደቱ በፊት ህመምተኛው ለስድስት ሰዓታት ምንም ነገር እንዳይበላ እና እንዳይጠጣ ይደረጋል፡፡ ማንኛውንም መድሃኒት የሚወስዱ ከሆነ ለሐኪምዎ ምን መድሃኒት እንደሚዎስዱ ማሳዎቅዎን እርግጠኛ ይሁኑ ከዛም ከልብ ካቴተራይዜሽን በፊት መቋረጥ ካለባቸው ያሳውቁዎታል፡፡

ታካሚው ምን ያጋጥመዋል?

ሐኪሙ ምርመራው ከመጀመሩ በፊት የልብ ምትዎን እና የደም ግፊትዎን ያረጋግጣል፡፡ የልብ ካቴተራይዜሽን (Cardiac Catheterization) እንደ ሕክምና ታስቦ ከሆነ እየተከናወነ ያለው ሙሉ ማደንዘዣ ሊያስፈልግዎት ይችላል፡፡ ለምርመራ ከሆነ ደግሞ ቦታው ላይ ብቻ ህመም እንዳይሰማ ማደንዘዣ በካቴተር መግቢያ አካባቢ ይሰጣል፣ እንዲሁም መጠነኛ ሰመመን ውስጥ እንዲሆኑ ይደረጋል።

ኢንፌክሽን ለመከላከል እንዲረዳ ካቴተር የሚገባበትን ቦታ መላጨት ሊያስፈልግ ይችላል፣ ከዚያም ማደንዘዣ መርፌ ቦታው ላይ ይወጋል እንዲሁም አካባቢው በፀረ ጀርም እንዲፀዳ ይደረጋል፡፡

ማደንዘዣው አካባቢውን ካደነዘዘው በኋላ የደም ስሩን ለማግኘት ትንሽ መቅደድ ያስፈልጋል፡፡ የፕላስቲክ ሽፋን በደም ሥሩ ውስጥ እንዲገባ ከተደረገ በኋላ ካቴተሩ በፕላስቲ ሽፋኑ ውስጥ ገብቶ ሐኪሙ ሊመረምርበት ወደሚፈልገው ቦታ እስኪደርስ ድረስ በደም ሥር ውስጥ እንዲሄድ ይደረጋል፡፡ በምርመራ ወይም በህክምና ሂደቱ ወቅት በሰውነትዎ ውስጥ የሚዘዋወረው ካቴተር ሲንቀሳቀስ ምንም ዓይነት የእንቅስቃሴው ስሜት ሊሰማን አይገባም፡፡

የልብ ካቴተራይዜሽን (Cardiac Catheterization) ሂደቱ ከተጠናቀቀ በኋላ እስክናገግም የተወሰነ ሰዓታት በሆስፒታል ውስጥ መቆየት ያስፈልጋል፡፡ የፕላስቲክ ሽፋኑ ከተወገደ በኋላ በማስገቢያ ቦታዎች ላይ ግፊት እንዲፈጠር ይደረጋል።

የልብ ካቴተራይዜሽን ሂደቱ ለምርመራ ታስቦ ከተከናወነ ምርመራው እንዳለቀ ለጥቂት ሰዓታት በሆስፒታል ከቆዩ በኋላ ወደ ቤት መሄድ ይችላሉ፡፡ ለሕክምና ተግባር የተከናዎነ ከሆነ ደግሞ የሕክምናው ክብደት እና የዶክተርዎ ውሳኔ ከሆስፒታል የሚወጡበትን ጊዜ የሚወስኑ ጉዳዮች ይሆናሉ፡፡

ለልብ ካቴተራይዜሽን (Cardiac Catheterization) የቬጅታኒ ሆስፒታልን ምርጫዎ ያድርጉ

ቬጂታኒ ሆስፒታል በዚህ ዘመናዊ አሰራር ውስጥ ለብዙ ዓመታት የዳበረ ሙያዊ ልምድ ያለው የልብ ህክምና ማዕከል አለው፡፡ ለልብ ካቴተራይዜሽን የሚያበቁ ምክንያቶች እንዳሉ ከተሰማዎት ዛሬውኑ ወደ ቬጂታኒ ሆስፒታል በመደዎል ከልብ ሐኪም ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ ይያዙ፡፡

  • Readers Rating
  • Rated 5 stars
    5 / 5 (2 )
  • Your Rating