BPH (Benign Prostate Hyperplasia) ይህ ችግር 80 ፐርሰንት የሚሆኑት ወንዶች እድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ የፕሮስቴት እጢያቸው መጠኑ እያደገ በመሄድ ሽንት መሽናትን አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡ በዚህም ምክኒያት ታማሚዎች የሽንት ፍሰት ዝግ ማለት ምልክቶቹን ስንመለከት የሽንት ፍሰት ዝግ ማለት የሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት ማታ ማታ ለሽንት ከአንድ ጊዜ በላይ መነሳት የሽንት ማጣደፍ መጨረሻ ላይ የሚወጣው ሽንት መንጠባጠብ ወይም መቆራረጥ
የፕሮስቴት እጢ ማደግ ችግርን ለመመርመር በቅድሚያ ሀኪሙ ታካሚውን ስለሚሰሙት ስሜቶች አንዳንድ ጥያቄዎች ከጠየቀ በኋላ አካላዊ ምርመራ ያደርጋል ከዚያ በመቀጠልም የሬክተም ምርመራ የሽንት ምርመራ እና የፕሮስቴት ሆርሞን መጠንን የሚያሳየን ፕሮስቴት ስፔሲፊክ አንቲጅን የሚባለውን የደም ምርመራ ነው፡፡ከነዚህ ምርመራዎች በኋላም ሀኪሙ እንደአስፈላጊነቱ የታካሚውን የየእለት የሽንት መጠን እና የሽንት ፍሰት ፍጥነትን መለካት እንዲሁም የፕሮስቴት እጢ ናሙና ምርመራን ሊያዝ ይችላል፡፡
ህመሙ እየባሰ የሚሄድ ከሆነና የታማሚውን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ የሚረብሽ ከሆነ ሀኪሙ የተወሰነ የፕሮስቴት እጢን በቀዶ ጥገና ሊየወጣ ይችላል፡፡የፕሮስቴት እጢን በሌዘር በታገዘ ቀዶ ጥገና ማስተካከል የሚቻል ሲሆን ይህም ከተለመደው የቀዶ ጥገና ቴክኒክ የተሻለ ውጤት ያስገኛል ይህም ሲባል የቀነሰ የደም መፍሰስ እንዲሁም ቶሎ የማገገም ሁኔታን ያመቻቻል ማለት ነው፡፡ይህ የህክምና አይነት በተለይም የደም ማቅጠኛ ለሚወስዱ ሰዎች እንዲሁም የደም መርጋት ችግር ላለባቸው ሰዎች አይነተኛ አማራጭ ነው፡፡