እንደ የአለም ጤና ድርጅት ዘገባ ካንሰር ለሞት ከሚዳርጉ አደገኛ በሽታዎች ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል ከዚህም ውስጥ በ2015 ከ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን በላይ ዜጎችን መቅጠፉ ይታወቃል
የሳምባ ካንሰር ማለት በሳምባ ውስጥ ጤነኛ ያልሆኑ ህዋሳት ከወስነት ቁጥጥር ውጪ መብዛት ሲሆን የእነዚህ ህዋሳት ከቁጥጥር ውጪ መብዛት የሳምባን የተለመደ አሰራር በማወክ ችግሩ ወደ ሌላ የሰውነት አካላት እንዲሰራጭ ምክኒያት ይሆናል
በአጠቃላይ ሁለት አይነት የሳምባ ካንሰር አይነቶች ሲኖሩ እነዚህም፡-
NSLC (Non Small Cell Lung Cell) ይህ አይነቱ የሳምባ ካንሰር በጣም የተለመደው ሲሆን ከ85-90 ፐርሰንት ይይዛል ከ SCLC ጋር ሲነጻጸር ስርጭቱ እና እድገቱ ዝግ ያለ ነው
SCLC( Small Cell Lung Cancer) ከ 10-15 ፐርሰንት የሚሆኑት የሳምባ ካንሰር አይነቶች ከዚህ ምድብ የሚገኙ ሲሆን ከመጀመሪያው ጋር ሲነጻጸር እድገቱም ሆነ ስርጭቱ ፈጣን እንደሆነ ይነገራል
ለህመሙ ተጋላጭ የሚያደርጉ ምክኒያቶችን ስንመለከት
ሲጋራ ማጨስ
የአየር ብክለት
በቤተሰብ አባል ተጋላጭነት ካለ እና እድሜ ይጠቀሳሉ
የበሽታው ምልክቶች
- የጠና ሳል
- ደም የቀላቀለ አክታ
- የጠና ትኩሳት
- የድምጽ መቀየር
- የአተነፋፈስ ችግሮች
- የደረት ህመም
- የበረታ ድካም
- ክብደት መቀነስ
የሳንባ ካንሰር ልየታ
በአጠቃለይ የሳምባ ካንሰር በሽታ በጊዜ ከተደረሰበት ማከም ሲሆን አሁን አሁን እድሜያቸው ከ55-75 ዓመት ለሆኑና በአመት 30ፓኮ ለሚያጨሱ አዋቂዎች መጠኑ ቀነስ ያለ CT-SCAN Test በሚባል የምርመራ አይነት በመረዳት በሽታው መኖር አለመኖሩን የሚያሳዩ ጠቋሚ ምልክቶችን ማግኘት እንችላለን
ዶ/ር ያዳ ሉዊስቻሮይን
የሳምባ እና ተያያዥ ችግሮች ስፔሻሊስት
የውስጥ ደዌ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ (ቬጂታኒ ሆስፒታል ባንኮክ)
መደበኛ የአገልግሎት ሰአት ዘወትር ከጠዋቱ 2፡00-2፡00(ምሽት)
የአማርኛ ቋንቋ የስልክ መስመራችን: +66909072560
ኢ-ሜይል: [email protected]
ስለ ሌሎች የካንሰር አይነቶች ለምሳሌ ስለ ሉኪሚያ መረጃ ለማግኘት ይሄን ይጫኑ ወይም በስልክ ይደውሉ + 66-2-734-0000 ext. 2960 ፣ 2961
- Readers Rating
- Rated 5 stars
5 / 5 (Reviewers) - Spectacular
- Your Rating