በጊዜ ከታወቀ መታከም የሚችለው ሊምፎማ - Vejthani Hospital

የጤና መረጃዎች

በጊዜ ከታወቀ መታከም የሚችለው ሊምፎማ

Share:

እንደሚታወቀው የካንሰር በሽታ በአለም አቀፍ ደረጃ ብዙ ሰዎች በመግደል ቀዳሚ መሆኑ ይታወቃል፡፡ሊምፎማ በታይላንድ ሀገር ከሚታዩት የካንሰር ህመሞች ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዝ ህመሙም በማንኛውም እድሜ ክልል ሊከሰት ይችላል፡፡ይህ የካንሰር አይነት በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ የበሽታ መከላከያ ህዋሶቻችንን የሚያጠቃ ሲሆን አንዳንዴም ከሊምፍ ኖዶች ውጪ ወደ ሌላ የሰውነታችን ክፍል ሊሰራጭ ይችላል፡፡ነገር ግን ይህ የካንሰር አይነት በጊዜው ከታከመ የበሽታው ደረጃ ከፍተኛ ቢሆንም እንኩዋን የመዳን እድል ይኖረዋል፡፡

ሊምፎማ ምንድነው ?

ሊምፎማ ማለት ሊምፎሳይት ከሚባሉት የነጭ ደም ህዋሳት የሚነሱ የደም ካንሰር ህመሞችን የሚያጠቃልል ህመም  ነው፡፡ሊምፋቲክ ሲስተም በዋናነት የተዋቀረው ከሰውነታችን በሽታ መከላከያ ህዋሳት ሲሆን ህመሙ አንዴ ከያዘ በደም አማካኝነት በቀላሉ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች በተለይም ወደ ጉበት፤ መቅኔ እና ሳምባ በፍጥነት ይሰራጫል፡፡

በአብዛኛው የሊምፎማ መምጫ ምክኒያት የማይታወቅ ሲሆን አንዳንዶቹ ለበሽታው ሊያጋልጡን የሚችሉ ነገሮችን ስናይ እንደ ኤች አይ ቪ ቫይረስ ፤ በዘር የሚተላለፍ በሽታ፤ እንዲሁም የሰውነት አካል ንቅለ ተከላ ያደረጉ ሰዎች የሚወስዷቸው መድሃኒቶች አይነት የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም የሚቀንሱ ሁኔታዎች ለበሽታዉ ተጋላጭነትን ይጨምራሉ፡፡

መከታተል ያለብን ጠቃሚ ምልክቶች 

  • የንፍፊት ማበጥ
  • ትኩሳት
  • ሳል
  • ትንፋሽ ማጠር
  • ማታ ማታ ማላብ
  • ክብደት መቀነስ
  • የሰውነት ማሳከክ

ሀኪሙ የንፍፊት ማበጥን ጨምሮ አጠቃላይ አካላዊ ምርመራ ያደርጋል በዚህም ወቅት በኢንፌክሽንም ሆነ ካንሰሩ በመሰራጨቱ ምክኒያት የንፍፊት ማበጥ የሚኖር ከሆነ በመርፌ በመታገዝ ናሙና መወሰድ ይኖርበታል፡፡

ምርመራ እና የህክምናው ሂደት

ለእያንዳንዱ የካንሰር አይነት እና እንደ በሽታው ደረጃ የሚሰጠው የህክምና አይነት የሚለያይ ሲሆን እንደ ህመሙ አይነት የጨረር ህክምና ፤የመድሃኒት ህክምና እንዲሁም የስቴም ሴል ንቅለ ተከላ ሊደረግበት ይችላል፡፡

እዚህ ጋር ሊሰመርበት የሚገባ ጉዳይ የሊምፎማ ህመም በጊዜ ከተደረሰበት መታከም የሚችል ሲሆን ምልክቱ የሚኖርዎት ከሆነ በአፋጣኝ ሀኪም ዘንድ መሄድ እንዳለብዎ አይርሱ፡፡

ተያያዥ የካንሰር መረጃዎች ለምሳሌ ስለ የትልቁ አንጀት ካንሰር መረጃ ለማግኘት ይሄን ይጫኑ ወይም በስልክ  ይደውሉ  + 66-2-734-0000 ext. 2960 ፣  2961

  • Readers Rating
  • Rated 2.7 stars
    2.7 / 5 (3 )
  • Your Rating