ታይሮድ በፊት ለፊት አንገታችን ላይ የሚገኝ እጢ ሲሆን ሰውነታችን በሁሉም መልኩ የተስተካከለ አሰራር እንዲኖረው የሚያደርጉ ሆርሞኖችን ያመርታል ይህ እንዲሆን ደግሞ “አዮዲን” የተባለ ንጥረ ነገር ያስፈልገዋል፡፡የአዮዲን መጠን አነስተኛ ወይም ከመጠን ማለፍ ደግሞ አጠቃላይ የሰውነታችንን ስርዓት ያውካል፡፡
የታይሮድ እጢ ጥቅሞች
- ለሰውነታችን እድገት እና መጎልበት
- ለአእምሮአችን ጤና ስሜታችንን ለማስተካከል
- የሰውነት ሙቀትን እንዲሁም አጠቃላይ አሰራር ለማስተካከል
- በጣም አስፈላጊ የሆኑ የሰውነታችን ክፍሎች እንደ፡- ልብ፤ጡንቻ፤እና አጥንትን የመሳሰሉ አካላት በትክክል እንዲሰሩ ለማድረግ
የታይሮድ እጢ በፍጥነት የሚሰራ ከሆነ ብዙ ሆርሞን በማምረት የሰውነታችንን ጤነኛ አሰራር እንዲታወክ ሊያደርግ ይችላል
ይህም ችግር “ሀይፐርታይሮይዲዝም” በመባል ይታወቃል፡፡ይህ ችግር ሲያጋጥም በእያንዳንዱ የሰውነታችን ክፍል ላይ የሚያሳየው ምልክት ከሰው ሰው ይለያያል፡፡
ሀይፐር ታይሮይዲዝም የሚያስከትላቸው ችግሮች
- ልብ፡- ድካም፤የተዛባ የልብ ምት እንዲሁም የልብ ህመም
- ስርዓተ ነርቭ ፡- የእጅ መንቀጥቀጥ፤ፍርሃት፤የእንቅልፍ ችግር፤እረፍት የማጣት ስሜት እና ትኩረት ማጣት
- ቆዳ፡- የቆዳ ማላብ፤የጸጉር መነቃቀል፤የታችኛው እግር ማበጥ፤የጥፍር መነቃቀል
- አይን፡- የአይን ኳስ ከተለመደው በላይ ወደ ፊት መውጣት እምባ መብዛት እንዲሁም መቆርቆር
- ሜታቦሊክ ሲስተም፡- የክብደት መቀነስ
- መራቢያ አካላት ላይ፡- የወር አበባ መዛባት ወይም የወር አበባ መቅረት
- ጡንቻ ላይ ፡- የጡንቻ መድከም እንዲሁም የእጅ መንቀጥቀጥ
- አንገት ፡- የታይሮድ እጢ በመጠን መተለቅ በዚህም ምክኒያት ደግሞ የአንገት ማበጥ
ታይሮቶክሲኮሲስ ምክኒያቶች
- ሀይፐርታይሮይዲዝም፡- የታይሮድ እጢ የታይሮድ ሆርሞንን ከመጠን በላይ ማምረት
- ታይሮዳይትስ፡- የታይሮይድ እጢ ብግነት እና በዚህም ምክኒያት ከመጠን ያለፈ ሆርሞን ማምረት
- የታይሮድ ሆርሞን እንዲጨምር አስተዋጽዎ ያላቸውን መድሃኒቶች መውሰድ
- በእርግዝና ምክኒያት በሚመጣ የጠና ህመም ምክኒያት ከመጠን ያለፈ የታይሮድ ሆርሞን መመረት
- አንዳንድ ፒቱታሪ እጢ ላይ የሚከሰቱ እባጮች
ታይሮቶክሲኮሲስ እንዴት ይታከማል
- መድሃኒቶች
- ራዲዮአክቲቭ አዮዲን ህክምና
- ቀዶ ጥገና
ሀኪሙ የታካሚውን እድሜ የሰውነት ሁኔታ እንዲሁም የበሽታውን ስፋት ከግምት ውስጥ በማስገባት አስፈላጊውን የህክምና አይነት የሚመርጥ ሲሆን ታካሚውም የታዘዘለትን መድሃኒት በአግባቡ በመውሰድ የአዮዲን መጠኑ ከፍ ያለ ምግብን በመቀነስ እና ሲጋራ ባለማጨስ ህክምናውን ማገዝ ይኖርበታል
ዶ/ር አሩን ኮንግቾ (በቬጂታኒ ሆስፒታል ኢንዶክሪኒሎጂስት)
[doctor_blog doctor_code=”91972″]
አጠቃላይ ጤናችን ላይ ችግር የሚያመጣው የታይሮድ ችግር
ዶ/ር አሩን ኮንግቾ (በቬጂታኒ ሆስፒታል ኢንዶክሪኒሎጂስት)
- Readers Rating
- Rated 2.8 stars
2.8 / 5 (Reviewers) - Good
- Your Rating