በእድሜ ጠና ያሉ ሰዎችን የሚያጠቃው “የአጥንት መሳሳት” - Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand.

የጤና መረጃዎች

በእድሜ ጠና ያሉ ሰዎችን የሚያጠቃው “የአጥንት መሳሳት”

Share:

በተለምዶ የአጥንት መሳሳት የምንለው አጥንታችን ጥንካሬውን አጥቶ ሲሳሳና በዚህም ምክኒያት የአጥንት መድከም ሲኖርነውበአብዛኛው ጊዜ ህመሙ ቢኖርም እንኳን ምንም ምልክት ስለማያሳይ እንዲሁም አንድ ሰው አጥንቱ ቢሳሳ እንኳን አጥንቱ መሳሳቱን ሊያውቅ ስለማይችል “ዝምተኛ ህመም” እንደሆነ ይታሰባል

የዚህ በሽታ ተጠቂዎች አጥንታቸው በቀላሉ የመሰበር አጋጣሚው ከፍተኛ ሲሆን ስብራት ካጋጠማቸው በኋላም ወደ ቀድሞ የተለመደ የእለት ተዕለት ተግባራቸው ለመመለስ ጊዜ ይፈጅባቸዋል፡፡በአጥንት መሳሳት ምክኒያት የሚፈጠር የአጥንት ስብራት በአብዛኛው የሚፈጠረው በዳሌ አካባቢ፤በአከርካሪ አጥንት ላይ እንዲሁም የሰዓት ማሰሪያ አንጓ ላይ ነው፡፡

ለዚህ በሽታ በይበልጥ ተጋላጭ የሆኑት እነማን ናቸው

  • እድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች እና ከ70 ዓመት በላይ የሆኑ ወንዶች
  • 45 ዓመት ሳይሞላቸው ያረጡ ሴቶች
  • ከዚህ በፊት የአጥንት ስብራት በተደጋጋሚ የገጠማቸው ሰዎች
  • ስቴሮይድ የሚባሉ የመድሃኒት አይነቶችን የሚጠቀሙ ሰዎች
  • የጠና ህመም ያለባቸው ሰዎች ለምሳሌ እንደ ኩላሊት ህመም

ምርመራ

ሰዎች የዚህ ህመም ተጠቂ መሆናቸውን ለማወቅ DEXA(Dual Energy X-Ray Absorp Hometry) የሚባል መሳሪያን በመጠቀም የአጥንት እፍጋትን መለካት ይቻላል ማለት ነው፡፡ ይህን ልኬት በመጠቀምም በዳሌ አጥንት፤አከርካሪ አጥንት እንዲሁም የሰዓት ማሰሪያ አንጓ አካባቢ ያለ የአጥንት እፍጋትን መለካት ይቻላል፡፡ስለዚህ ይህ ምርመራ የአጥንት ስብራት ሳይከሰት በፊት አጥንት መሳሳት መኖሩን የምናይበት ነው፡፡

የአጥንት መሳሳት ህክምና

  • የአጥንት መሳሳት ችግር ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ህክምና አማራጮችን ስንመለከት መድሃኒት መውሰድ እንዲሁም ጤነኛ የኑሮ ዘይቤን መከተል፤በቂ የካልሲየም ፤የቫይታሚን ዲ እንዲሁም የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ ያስፈልጋል
  • በአጥንት መሳሳት ምክኒያት የአጥንት ስብራት ቢገጥምዎ አፋጣኝ የህክምና እርዳታ ማግኘት ይኖርብዎታል

የተመጣጠነ ምግብ መመገብ እንዲሁም በቂ ካልሲየም እና ቫይታሚን ዲ ማግኘት

በየእለቱ መደበኛ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ

  • ሲጋራ ማጨስ እና አልኮል መጠጥ የመውሰድ ልምድን መቀነስ
  • የአጥንት እፍጋት ምርመራን ያካተተ መደበኛ የጤና ምርመራ ማድረግ የሚሉት ይጠቀሳሉ