የአለርጂ ችግር በብዛት በህጻናት ላይ የሚታይ ሲሆን የአለርጂ ምንጮችን ስናይ የመጀመሪያው ዘረ-መል ሲሆን ሁለተኛው የአየር እና የምግብ ብክለት ናቸው
የአለርጂን ስሜቶች እንዴት እንለያቸዋለን ?
- የቆዳ አለርጂ ፡- የቆዳ መድረቅ፤ በፊት ፤ በክርን እንዲሁም በጉልበት ላይ የሚወጣ ቀላ ቀላ ያለ ሽፍታ
- የምግብ አለርጂ ፡- ቆዳ ላይ የሚወጣ ሽፍታ፤ደም የቀላቀለ ተቅማጥ፤የመተንፈስ ችግር እንዲሁም አስም
- የመተንፈሻ አካላት አለርጂ ፡- በተለይ ወቅቶች ሲቀያየሩ የአፍንጫ ማፈን፤የአፍንጫ እና የአይን ማሳከክ፤ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ፤ማስነጠስ፤አስም፤ማታ ማታ ሳል፤ሲተነፍሱ ሲር ሲር የሚል ድምጽ
መከላከያ መንገዶች፡-በእርግዝና ጊዜ ጀምሮ በቫይታሚን እና ጠቃሚ ማዕድናት የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ ህጻኑ/ኗ ከተወለደች ጀምሮ ደግሞ ለተከታታይ ስድስት ወራት የእናት ጡት ወተት ብቻ መስጠት ከዚያ በኋላ እንደ ሩዝ፤አትክልት፤ፍራፍሬ፤የዶሮ ስጋ እና አሳ የመሳሰሉ ምግቦችን መመገብ ህጻናቱ እነዚህን ምግቦች ከተመገቡ በኋላ ከላይ የገለጽናቸው የአለርጂ ምልክቶች የሚከሰቱ ከሆነ ለይቶ መመልከት እና ወደ ሀኪም ዘንድ ማምራት ያስፈልጋል
ስለ ህፃናት ጤና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ለምሳሌ በህጻናት ላይ ስለሚታይ ማንኮራፋት መረጃ ለማኘት ይሄን ይጫኑ ወይም በስልክ ይደውሉ + 66-2-734-0000 ext. 2960 ፣ 2961
- Readers Rating
- Rated 3.3 stars
3.3 / 5 (Reviewers) - Very Good
- Your Rating