ስር የሰደደ የሆድ ህመም፣ ችላ ልንለው የማይገባ በሽታ ነው

የጤና መረጃዎች

ስር የሰደደ የሆድ ህመም፣ ችላ ልንለው የማይገባ በሽታ ነው

Share:

የሆድ ህመም

ኢንዶስኮፕ ማለት ትንሽ ፣ ተጣጣፊ ፣ የብርሃን ጨረር የሚያስተላልፍ ትቦ ሲሆን በላይኛው የስርአተ ልመት ክፍል ውስጥ በማስገባት ጨጓራን፣ ጉሮሮን እና የላይኛው የቀጭን አንጀት ክፍል ላይ ያለ በሽታን ለመመርመር የሚያገለግል መሳሪያ ነው፡፡  ለምሳሌ፦

  • ሥር የሰደደ የሆድ ህመም
  • በመደበኛነት የማቅለሽለሽ እና የማስታወክ ስሜት
  • የምግብ አለመፈጨት ችግር እና ሥር የሰደደ ልባችን ላይ የማቃጠል ስሜት
  • ለመዋጥ መቸገር
  • በሚያስታውከን ሰአት ደም መቀላቀል
  • ውስጥ  ላይ  በሚከሰት የደም መፍሰስ ምክንያት  የሚመጣ የደም ማነስ

የኢንዶስኮፒ ምርመራ  ቅደምተከተሎች እንደሚከተለው ተቀምጠዋል፦

  1. የኢንዶስኮፒ ምርመራው ከመደረጉ ከ 6 – 8 ሰዓታት በፊት ታካሚው ምግብ እና መጠጥ ማቆም አለበት
  2. ታካሚው የኢንዶስኮፒ ምርመራው ከማድረጉ ቢያንስ ከ7 -10 ቀናት ቀድሞ የተወሰኑ ዓይነት መድሃኒቶችን መውሰድ ማቆም አለበት ፡፡
  3. ሐኪሙ የኢንዶስኮፒ ምርመራው እንዴት እንደሚከናወን እንዲሁም ስለሚከሰቱ ችግሮችና የጎንዮሽ ጉዳቶች በዝርዝር ያብራራል ፡፡
  4. ሐኪሙ የሚረጭ ወይም በመርፌ መልኩ የሚሰጥ ማደንዘዣ (local anesthetics) ለታካሚው በአንገቱ አካባቢ ይሰጠዋል  እዲሁም መለስተኛ የእንቅልፍ መድሃኒትም ይሰጠዋል፡፡
  5. የኢንዶስኮፒ ምርመራው 10 ደቂቃ ያህል ይወስዳል፡፡
  6. የኢንዶስኮፒ ምርመራው ካለቀ በኋላ ህመምተኛው ለማገገም ቢያንስ 30 ደቂቃ ማረፍ አለበት ፡፡
  7. ከኢንዶስኮፒ ምርመራው በኋላ ታካሚው በወሰደው የእንቅልፍ መድሃኒት ምክንያት የብዥታ እና የማዞር ስሜት ሊኖረው ይችላል ፡፡

ለበለጠ መረጃ የ Gastroenterology እና Hepatology ማዕከልን ያነጋግሩ ወይም በስልክ  ይደውሉ 
+ 66-2-734-0000 ext. 2960 ፣  2961

  • Readers Rating
  • Rated 4.3 stars
    4.3 / 5 (5 )
  • Your Rating