የልብ ቫልቭ በሽታ አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰተው እድሜያቸው ከ40 አመት በላይ በሆኑ ሰወች ላይ ነው ለዚህም ምክንያቱ የህብረ ህዋሳት (tissue) እንደፈለጉ አለመተጣጠፍ ችግር ሲሆን በጊዜ ሂደትም የልባችን ቫልቭ ትክክለኛ ቅርፁን በማሳጣትና የልብ በር በትክክል አልዘጋ እንዲል በማድረግ ደም ወደኋላ ተመልሶ እንዲፈስ ያደርጋል:: ይሄም ልባችን ተግባሩን በትክክል እንዳይሰራ የሚያደርግ ሲሆን የሚከተሉትን የሕመም ምልክቶች ያሳያል፦
- በቀላሉ መድከም
- ማዞር
- ራስን መሳት
- የደረት ህመም
- ልባችን በፍጥነት መምታት
- ጫማችን እና ቁርጭምጭሚት ላይ እብጠት
ከላይ የተገለፁት ምልክቶች ካለዎት ዶክተር ማየትና የልብ ምርመራ ማድረግ ይኖርብዎታል፡፡የልባችን በሮች በትክክል ባለመዘጋታቸው ምክንያት ደም ወደኋላ ተመልሶ የሚፈስ ከሆነ ሐኪሙ የልብን መደበኛ ሥራ ወደነበረበት ለመመለስ እናየበሽተኛውን ሕይወትን ለማትረፍ የልብ ቫልቭ ቀዶ ጥገና እንዲደርግ ይመክራል፡፡የልብ ቫልቭ ቀዶ ጥገና የተደረገለት ህመምተኛ የተሻለ ቀሪ ህይወት ይኖረዋል በተጨማሪም ልብ ውስጥ የሚፈጠር የደም መርጋት እንዲሁም በሰውነት ውስጥ ለሚፈተር የደም መፍሰስ ችግር የመጋለጥ እድሉ ይቀንሳል፡፡
- Readers Rating
- Rated 4.8 stars
4.8 / 5 (Reviewers) - Spectacular
- Your Rating