የዲስክ መንሸራተት ፣ የተለመደ የጀርባ ህመም መንስኤ ነው - Vejthani Hospital

የጤና መረጃዎች

የዲስክ መንሸራተት ፣ የተለመደ የጀርባ ህመም መንስኤ ነው

Share:

ከ 2 ሰዓታት በላይ ኮምፒዩተር እየተጠቀሙ መቀመጥ የጀርባ ህመም እና እግሮቻችን ላይ የመደንዘዝ ስሜትን ያስከትላል ፡፡  ብዙ ሰዎች ህመሙ ከፍቶ ወደ ዲስክ መንሸራተት እስከሚቀየርበት ጊዜ ድረስ ህመሙን ተቋቁመው ይቆያሉ።  

የቬጅታኒ ሆስፒታል የወገብና አከርካሪ አጥንት ሐኪም የሆኑት ዶክተር ፓታራ ኮሳነንት በበኩላቸው የዲስክ መንሸራተት ሊያስከትሉ ይችላሉ ብለው ካስቀመጧቸው ዋና ዋና ነገሮች ውስጥ ከባድ ነገሮችን ማንሳት ፣ መኪና ለሰዓታት ማሽከርከር ፣ ወደጎን መታጠፍና መጠምዘዝ ማብዛት፣ እንዲሁም የጀርባ አጥንት ላይ አደጋ ሲያጋጥም ፣  እነዚህ ችግሮች አኑለስ ፋይብሮሰስ የተባለውን የዲስኩን የውጨኛ ክፍል የማርጀት እና ጉዳት ከፍ ያደርጋሉ ​​በመጨረሻም የዲስክ መንሸራተት (herniated disc) ያመጣሉ።  

የዲስክ መንሸራተት የገጠማቸው በሽተኞች በጀርባቸው እና እግራቸው ላይ ህመም ይሰማቸዋል ብዙውን ጊዜ የቤት ውጭ እንቅስቃሴዎችን የሚሰሩ እና ከባድ የአካል እንቅስቃሴን በሚሰሩ ሰዎች፣ ወይም ለሰዓታት በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ ሳይንቀሳቀሱ ለረዥም ሰአት በሚቆዩ ሰዎች ላይ ፣ በተለይም ኮምፒተር በመጠቀም ለረዥም ሰአት ቢሮ ላይ የሚቀመጡ ኦፊሰሮች የችግሩ ተጠቂ ናቸው፡፡ የዲስክ መንሸራተት ችግር ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው ዕድሜያቸው ከ 40 ዓመት በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ ነው ፣ እንዲሁም የሰውነት ክብደታቸው ከፍተኛ የሆኑ ሰዎች የጀርባ አጥንታቸው የሰውነታቸውን ክብደት ስለሚሸከም፣ የዲስክ ማርጀትና በመጨረሻም ወደ ዲስክ መንሸራተት ያመራል ሲሉ ዶክተር ፓታራ ይመክራሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የዲስክ መንሸራተት ህመምን የጀርባ አጥንት ቀዶ ጥገና በማድረግ ማከም ይቻላል፣ ውጤታማ በሆነና ደህንነቱ የተጠበቀ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ማለትም ማይክሮስኮፕ ወይም ኢንዶስኮፕ በመጠቀም ሰውነታችን ትንሽ ቦታ ላይ ለህክምና መሳሪያው ማስገቢያ ብቻ በመክፈት የሚደረግ ቀዶ ጥገና ነው፡፡ ይሄ ዘዴ ከህክምናው ጋር ተያይዞ የሚፈጠርን የደም መፍሰስና የጡንቻ ህመም ይቀንሳል፣ እንዲሁም ከባህላዊው የቀዶ ጥገና ሕክምና ጋር ሲነፃፀር ቶሎ ያገግማል፡፡ ከላይ ከተጠቀሰው ቴክኖሎጂ በተጨማሪ ፣ኢንትራኦፕሬቲቭ ኒውሮሞኒተሪንግ (Intraoperative Neuromonitoring) ቴክኖሎጅ ይጠቀማል ይሄም በእውነተኛ ጊዜ (real-time) የሚሰራ ሲሆን በቀዶ ጥገና ወቅት ነርቮችን ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ይቆጣጠርልናል፣ በመሆኑም በቀዶ ጥገናው ወቅት ሊከሰት የሚችለውን የነርቭ ጉዳት ይቀንሳል፡፡

  • Readers Rating
  • Rated 3.3 stars
    3.3 / 5 (10 )
  • Your Rating