የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ ጠቃሚ ነውን? - Vejthani Hospitala

የጤና መረጃዎች

የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ ጠቃሚ ነውን?

Share:

የማህፀን በር ካንሰር በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ በጣም የተለመደ የካንሰር ዓይነት ሲሆን ምልክት ሳያሳይ የሴቶችን ጤና አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ነው፡፡ በቀን ውስጥ 14 የሚያህሉ ሴቶች በማህፀን በር ካንሰር ይሞታሉ። ስለዚህ የተሻለ መፍትሄ እና ህክምናን ለማግኘት እንዲሁም ችግሩ የከፋ ደረጃ ላይ ሳይደርስ ለማወቅ የማህጸን ካንሰር ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

በቬጂታኒ ሆስፒታል የወሊድ እና አጠቃላይ የእናቶች ጤና ሐኪም የሆኑት ዶክተር ቻሊዳ ራኦራንግሮት እንደገለፁት የማህፀን በር ካንሰር የሚመጣው HPV 16 እና 18 በሚባሉ የሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ ኢንፌክሽን ምክንያት ነው፡፡ አብዛኛዎች የሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ ኢንፌክሽን የሚከሰቱት በጾታዊ ግንኙነት ወቅት ነው። ብዙ የወሲብ ጓደኛ መኖር ወይም ቀድሞ የወሲብ ግንኙነት መጀመር ለበሽታው ያለንን ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ምክንያቶች ናቸው፡፡ በመሰረቱ የማህፀን በር ካንሰር በመጀመሪያዎቹ ደረጃ ላይ እያለ ምንም ዓይነት ምልክት አያሳይም ነገር ግን የማህፀን በር ካንሰር
ምርመራ በማካሄድ ማወቅ ይቻላል፡፡ በተወሰኑት ሴቶች ላይ ብልት ውስጥ ያልተለመደ የደም መፍሰስ ፣ በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት ደም መፍሰስ፣ ወይም ያልተለመደ የብልት ፈሳሽ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ የማህፀን በር ካንሰር ሌሎች ምልክቶችንም ያሳያል እነሱም የእግሮች እብጠት ፣ የሊንፍኖዶች እብጠት(Lymphadenopathy)፣ የኩላሊት በሽታ እዲሁም ሽንት እና ሰገራ ላይ ደም መቀላቀል ናቸው።

የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ እያንዳንዱ ሴት ልታስብበት የሚገባና የተሻለ የመከላከያ ዘዴ ነው። በተለይም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ የጀመሩ ሴቶች የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ ማድረግ አለባቸው ፡፡ ይሁን እንጂ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ያልጀመሩ ሴቶችም ቢሆን ዕድሜያቸው ከ30 ዓመት በላይ ከሆነ የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት 3 ዓይነት የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ ዘዴዎች አሉ እነሱም፦

የፓፕ ምርመራ(Pap Smear)

  • ጤነኛ ያልሆኑ ህዋሶች መኖራቸውን ለመመርመር የማህጸን አንገት ላይ ናሙና በመውሰድ በማይክሮስኮፕ ስላይድ ላይ በማስቀመጥ ለምርመራ ይዘጋጃል፡፡

Liquid Based Cytology

  • ያልተለመዱ ህዋሳት መኖራቸውን ለመመርመር የማህጸን አንገት ላይ ናሙና በመውሰድ በውስጡ የማቆያፈሳሽ የያዘ ጠርሙስ ውስጥ ይቀመጣል ፡፡ ይህ ዘዴ የተሻለና ትክክለኛ ውጤትን ይሰጣል፡፡

የሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ(Human papillomavirus)ምርመራ

  • ይህ ዘዴ በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭነትን የሚጨምሩትን የሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ መኖራቸውን ለማረጋገጥየሚደረግ ምርመራ ሲሆን የምርመራ ውጤቱም የተሻለና ትክክለኛ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ዘዴ አብዛኛውን ጊዜከLiquid Based Cytology ዘዴ ጋር በማቀናጀት የሚደረግ ምርመራ ነው።

“የማህፀን በር ካንሰር መከላከል ከምንችላቸው የካንሰር ዓይነቶች ውስጥ አንዱ ነው። የተሻለው የመከላከያ ዘዴም ወደ ካንሰርነት ከመቀየሩ በፊት ለማወቅ የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ ማድረግ ነው። የፓፕ ምርመራ እና Liquid based cytology ምርመራ በዓመት አንድ ጊዜ እንዲደረግ ይመከራል እንዲሁም የሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ ምርመራ በየ3 ዓመቱ እንዲደረግ ይመከራል፡፡ ይሁን እንጂ ሁሉም ሴቶች ከእናቶች ጤና ጋር ተያያዥ የሆኑ ችግሮችን ለማወቅ በየአመቱ ምርመራ ማድረግ እንዳለባቸው” ዶክተር ቻሊዳ ይናገራሉ፡፡

በተጨማሪም ፀረ-ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ(HPV)ክትባት መከተብ ከማህፀን በር ካንሰር መከላከያ አማራጮች አንዱ ነው፡፡ ዕድሜያቸው ከ9 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆች ክትባቱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ዕድሜያቸው ከ9 እስከ 15 ዓመት ለሆኑ ሕፃናት ዶክተሩ 2 ኢንጀክሽን እንዲከተቡ ይመክራል። ነገር ግን እድሜያቸው ከ15 እስከ 45 ዓመት ዕድሜ ላላቸው ሰዎች ሐኪሙ 3 ኢንጀክሽን እንዲከተቡ ይመክራል ፡፡ ለዚህም ዋነኛ ምክንያቱ ክትባቱ ከአዋቂዎች ይልቅ
በሕፃናት ላይ ውጤታማ በመሆኑ ነው። በመሆኑም ከልጅነት ጊዜ ጀምሮ 2 የክትባት ኢንጀክሽን መቀበልና በወጣትነት ወይም በአዋቂነት ዕድሜ 3 የክትባት ኢንጀክሽን ከመቀበል ጋር እኩል ነው፡፡ ክትባቱ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ባላደረጉ ሰዎች የበለጠ ውጤታማ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ሲፈጽመው የነበሩ ሰዎችም ክትባቱን መውሰድ ይችላሉ፡፡

ለማጠቃለል ያህል የማህፀን በር ካንሰርን ለመከላከል የመለያ ምርመራ ማድረግ በሃኪም የሚመከርና ለሁሉም ህመምተኛ ጥሩ እና ተገቢ የሆነ የመከላከያ ዘዴ ነው፡፡

  • Readers Rating
  • Rated 3.8 stars
    3.8 / 5 (11 )
  • Your Rating




Related Posts