የስንፈተ ወሲብ (Erectile Dysfunction) ችግር? መጨነቅ አያስፈልግም ! መታከም ይችላል!

የጤና መረጃዎች

የስንፈተ ወሲብ (Erectile Dysfunction) ችግር? መጨነቅ አያስፈልግም ! መታከም ይችላል!

Share:

አብዛኛወች ወንዶች ጠዋት ላይ ብልት አለመቆምን ማስተዋል፣ ብልትን ለማቆም መቸገር ወይም የግብረ ስጋ ግንኙነት ለማድረግ በሚያስችል መልኩ መቆም አለመቻል፣ ወይም የግብረስጋ ግንኙነት ፍላጎት መቀነስ አይነት ችግሮችን ያስተውላሉ። እነዚህ የስንፈተ ወሲብ (Erectile Dysfunction) ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ። ወንዶች ያማረ የወደፊት ህይወት እንዳይኖራቸው እንደሚያደርግ አመላካች ነው።

የስንፈተ ወሲብ ችግር (Erectile Dysfunction) እድሜያቸው ከ20-30 ከሚሆኑት ወንዶች ውስጥ 8% የሚሆኑትን እንደሚያጠቃና እድሜያቸው ከ70-75 ከሆኑት ላይ ደግሞ ወደ 37% ከፍ እንደሚል ተመራማሪዎች አረጋግጠዋል። ይሁን እንጂ ስንፈተ ወሲብ (Erectile Dysfunction) በአሁኑ ሰአት በደንብ የሚታወቅና የተለያዩ የህክምና አማራጮችም ያሉት ችግር ነው።

ስንፈተ ወሲብ (Erectile Dysfunction) በምን ይመጣል?

  • የእድሜ መግፋት
  • ዝቅተኛ ቴስቴስትሮን
  • ጭንቀት፣ ፍርሃት ወይም ድብርት
  • በቂ እንቅልፍ አለማግኘት
  • ሲጋራ ማጨስና አልኮል መጠጥ

ሌሎች የጤና ችግሮች በተለይ የደም ግፊት፣ የስኳር በሽታ፣ ከፍተኛ ኮሌስትሮል

ስንፈተ ወሲብን እንዴት ማከም ይቻላል?

የስንፈተ ወሲብ ህክምና እንደ ችግሩ መንስዔ እና እንደችግሩ ክብደት ይለያያል። የህክምና አማራጮች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • የመድሃኒት ህክምና፡ መድሃኒቶች የደም ፍሰትን ይጨምራሉ እንዲሁም የፆታዊ ፍላጎት በሚኖርበት ጊዜ ብልት በምላሹ እንዲቆም የሚያደርጉ ናቸው። አብዛኛዎች የስንፈተ ወሲብ መድሃኒቶች ስራቸውን ለመጀመር 30 ደቂቃ አካባቢ ይወስድባቸዋል። ሊያጋጥሙ የሚችሉ የጎንዮሽ ጉዳቶችም ራስ ምታት፣ አፍንጫችን ድፍን የማድረግ፣ የቆዳ መቅላት፣ የእይታ መቀየር ወዘተ ሊኖሩ ይችላሉ።
  • ኤክስትራፖሬሽን ሾክዌቭ ህክምና (Extracorporeal Shockwave Therapy): ይህ ህክምና ለስንፈተ ወሲብ አዲስ የህክምና አማራጭ ነው። ይህ የህክምና ዘዴ ታካሚው ብልቱን በበቂ ሁኔታና በራሱ ሰዓት መቆም እንዲችል ያደርገዋል። የሾክዌቭ ህክምና ሂደት የደም ዝውውርን በመጨመርና የደም ስሮች በአዲስ መልኩ ተግባራቸውን እንዲያከናውኑ በማነቃቃት የተሻለ የደም ፍሰት እንዲኖር ያደርጋል ይሄም የፆታዊ ግንኙነት አቅም እንዲመለስ እንዲሁም እንዲሻሻል ያግዛል።
  • ቴስቴስትሮንን የመተካት ህክምና (Testosterone Replacement Therapy)፡ ዝቅተኛ የቴስቴስትሮን መጠን ያላቸው ወንዶች ቴስቴስትሮን የመተካት ህክምና በማግኘት ወንዶች የተሻለ ፆታዊ መነሳሳት እንዲኖራቸው ማድረግ ይቻላል። የሆርሞን ህክምና አብዛኛውን ጊዜ ዳሌ አካባቢ በመርፌ መልኩ ይሰጣል። ቴስቴስትሮንን ለመተካት ከሚደረጉ ህክምናዎች በብዛት የተለመዱት የቴስቴስትሮን አይነቶች ‘Cypionate’ እና ‘Enanthate’ ናቸው። ቴስቴስትሮን cypionate የተባለው መድሃኒት ግማሽ ላይፉ (half-life) 2 ሳምንት ሲሆን በአንፃሩ ቴስቴስትሮን enanthate የሚባለው ከ10-12 ሳምንት half-life አለው። ሌላኛው ቴስቴስትሮን የሚተካ መድሃኒት አወሳሰድ መንገድ በሚቀባና ቆዳን ሰርጎ መግባት በሚችል በቅባት መልኩ ነው። ይህም ሆርሞኑ በቆዳችን ሰርጎ ከገባ በኋላ በደማችን ውስጥ ስራውን ያከናውናል።

ይሁን እንጂ የአኗኗር ዘይቤን ማስተካከል ያስፈልጋል ምክንያቱም ጤናማ ያልሆኑ ልምዶች ስንፈተ ወሲብን ያባብሳሉ።ያስታውሱ በየቀኑ እስፖርታዊ እንቅስቃሴ ያድርጉ፣ ክብደትወን ይቀንሱ፣ ሲጋራ ማጨስ ያቁሙ፣ የአልኮል መጠጥ ይቀንሱ፣ ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች ያስወግዱ፣ ጤናማ ምግቦችን ይመገቡ፣ ጭንቀትን ይቀንሱ። ስንፈተ ወሲብ ያለብዎት ከመሰለዎ ዶክተር ማማከር በጣም አስፈላጊ ነው። ማፈር የለብዎትም!

  • Readers Rating
  • Rated 3 stars
    3 / 5 (48 )
  • Your Rating