አምስቱ ስንፈተ ወሲብን የምናክምባቸው መንገዶች

የጤና መረጃዎች

አምስቱ ስንፈተ ወሲብን የምናክምባቸው መንገዶች

Share:

ስንፈተ ወሲብ (Impotence)ወይም የወንድ ብልት አለመቆም ችግር ለወንዶች አሳሳቢ ከሆኑ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው። ይህ ችግር የወንዶችን በራስ መተማመን የሚቀንስና ፍርሃት የሚያሳድር ነው። ስንፈተ ወሲብ (Impotence) ማለት በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የወንድ ልጅ ብልት በደንብ መቆም አለመቻል ነው።

አያሳስባቹ! ስንፈተ ወሲብን (Impotence) ማከም የምንችልባቸው ብዙ መንገዶች አሉ።

  • ብዙ ስኳርንና ከፍተኛ ካርቦሀይድሬት ያላቸውን ምግቦች ማስወገድ። ምክንያቱም እነዚህ ስኳር የበዛባቸው ምግቦች የወሲብ መነሳሳትን ወይም የወሲብ ፍላጎትን ሊቀንሱ ይችላሉ።
  • የኮሌስትሮል መጠናችን ጤነኛ በሚባለው ደረጃ መቆጣጠር።
  • የደም ፍሰትን ለመጨመር ከፍተኛ አሚኖ አሲድ (Arginine) ያላችው ምግቦችን መጠቀም።
  • በዚንክ የበለፀጉ ምግቦችን መጠቀም እንዲሁም የቴስቴስትሮን ሆርሞን እንዲመረት የሚረዱ ሰፕልመንቶችን መውሰድ።
  • ከፍተኛ ፍላቮኖይድ ያላቸውን ምግቦች መመገብ፣ ይህ ንጥረነገር በታይላንድ ከዕፅዋት በተለይም የታይላንድ ጥቁር ዝንጅብል (Kaempferiaparviflora) ላይ እናገኛለን። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ፍላቮኖይድ ብዙ የጤና ጥቅሞች ያሉት ሲሆን ብልት ላይ ያሉ የደም ስሮች ከንደገና እንዲያገግሙ ይረዳል።

ይሁን እንጂ አሳሳቢ የሆነ ስንፈተ ወሲብ(Impotence) ችግር ካለብዎ የሜዲካል ህክምና ማግኘት በተጓዳኝም ጤናወትን መጠበቅ ይኖርብወታል። አሁን ላይ ስንፈተ ወሲብን(Impotence) በውጤታማነት ማከም የሚያስችል አዲስ ኢኖቬቲቭ የሜዲካል ህክምና አለ። ይሄም ኤክስትራኮርፖራል ሾክዌቭ ህክምና (Extracorporeal Shockwave Therapy) ይባላል።

የኤክስትራኮርፖራል ሾክዌቭ ህክምና የታካሚው ብልት ውግት አድርጎ በመያዝ ዝቅተኛ ኢንተንሲቲ ባለው ግፊተ ሞገድ ወደ 4000 ሾክ በወንዱ ብልት 4 ቦታ ላይ የብልት የደምስሮችን ለማነቃቃት ይሰጣል። በዚህ ህክምና ታካሚው በሳምንት ከ1-2 ጊዜ በተከታታይ ለ12 ሳምንት ህክምናውን መውሰድ አለበት። 

ለተጨማሪ መረጃ እባክዎ ያነጋግሩን 

ቬጅታኒ ሆስፒታል Q-Life ማእከልን፣ 11ኛ ፍሎር፣ ቬጅታኒ ሆስፒታል ያነጋግሩ ወይም በስልክ ቁጥር +66(0)2-734-0000 ext. 1125 ይደውሉ።

  • Readers Rating
  • Rated 2.7 stars
    2.7 / 5 (15 )
  • Your Rating


Tags: