የሳምባ ካንሰር (Lung cancer) በጊዜ ከተደረሰበት ሊድን ይችላል - Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand.

የጤና መረጃዎች

የሳምባ ካንሰር (Lung cancer) በጊዜ ከተደረሰበት ሊድን ይችላል

Share:

የሳንባ ካንሰር (Lung cancer) ከቁጥጥር ውጭ በሆነ የሳንባ ሕዋሳት መመረት ምክንያት የሚመጣ በሽታ ሲሆን በመጨረሻም ካንሰራማ የሆነ የሳንባ እጢ በመመስረት የሳንባው ተግባር ይቀንሳል፡፡ እንደ ክብደቱ ዓይነት የሳንባ ካንሰር በ2 ይከፈላል እነሱም:-

  • Non-Small Cell Lung Cancer ይህ አይነቱ የሳምባ ካንሰር በጣም የተለመደ ነው። ከ85-90 ፐርሰንት የሚሆኑት የሳንባ ካንሰር በሽተኞች የዚህ ዓይነቱ ተጠቂ ናቸው። የካንሰር ህዋስ ስርጭቱ እና እድገቱ ፈጣን ስላልሆነ ቀድሞ ከታወቀ መዳን ይችላል።
  • Small Cell Lung Cancer አልፎ አልፎ የሚከሰት የሳንባ ካንሰር ዓይነት ነው። ከ10-15 ፐርሰንት የሚሆኑት የሳምባ ካንሰር በሽተኞች ላይ ብቻ ይከሰታል። የካንሰር ህዋሱ እድገትና ስርጭት በጣም ፈጣን ስለሆነ የዚህ ዓይነት ካንሰር የተገኘባቸው በሽተኞች በቶሎ ይሞታሉ።

ሁሉም ሰው እንደሚያውቀው ሲጃራ ማጨስ የሳንባ ካንሰር ዋነኛ መንስኤ ነው። ይሁን እንጂ በጣም ብዙ የችግሩ መንስኤዎች አሉ ለምሳሌ ለኬሚካሎች እና ለካንሰር አምጭ ውህዶች መጋለጥ፣ የአየር ብክለት፣ ቤተሰብ ውስጥ ካንሰር ተጋላጭ ሰው ከነበረ፣እንዲሁም የእድሜ መግፋት ናቸው።

በዋናነት በመጀመሪያው ደረጃ ላይ ያለ የሳንባ ካንሰር ምንም አይነት ምልክቶችን አያሳይም ነገር ግን በመሰራጨት ደረጃ ላይ ካለ የሚከተሉትን ምልክቶች ያሳያል:-

  • የጠና ሳል
  • ደም የቀላቀለ አክታ
  • የአክታ መብዛት
  • የጠና ትኩሳት
  • የድምጽ መጎርነን
  • ለመተንፈስ መቸገር
  • የደረት ህመም
  • በቀላሉ መድከም
  • ክብደት መቀነስ

ዕድሜያቸው ከ55 እስከ 75 ዓመት የሆኑ እና በዓመት ከ30 በላይ ሲጃራዎችን የሚያጨሱ ሰዎች የሳንባ ካንሰርን ለመለየትና በሳንባ ውስጥ ለሚከሰቱ ማናቸውም ያልተለመዱ ችግሮች ለማዎቅ ዝቅተኛ ዶዝ ባለው ሲቲስካን ምርመራ እንዲያካሂዱ ይመከራል፡፡ ከዝቅተኛ ዶዝ ሲቲስካን በተጨማሪ የሳንባ ራጅ ምርመራ በሳንባዎች ውስጥ ያሉ ማናቸውም ችግሮች ለምሳሌ ነጠብጣቦች ወይም ዕጢዎችን መለየት ይችላል፡፡ በሳንባ ውስጥ ነጠብጣቦች ወይም ዕጢዎች ከተገኙ ሐኪሙ ባዮፕሲ ሊያዝ ይችላል። የሳንባ ካንሰር ገና በመጀመሪያ ደረጃው ከታወቀ ሊድን የሚችል በሽታ ነው፣ ነገር ግን ካንሰሩ ወደ ሌሎች አካላት ከተሰራጨ ማዳን ከባድ ይሆናል ምናልባትም ለሕይወት አስጊ ሊሆን ይችላል ፡፡ ስለሆነም ለሳንባ ካንሰር ተጋላጭ ከሆኑ ወይም እነዚህ የተጠቀሱ ምልክቶች ካሉዎት ወዲያውኑ ምርመራ ማድረግና ሕክምና ማግኘት ይኖርብዎታል፡፡

  • Readers Rating
  • Rated 3.5 stars
    3.5 / 5 (4 )
  • Your Rating