የጡት ካንሰር - Breast cancer - Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand.

የጤና መረጃዎች

የጡት ካንሰር – Breast cancer

Share:

የጡት ካንሰር (Breast cancer) ሴቶችን የሚያጠቃ በጣም የተለመደ የካንሰር አይነት ነው። የሴቶች እድሜ እየጨመረ በሄደ ቁጥር ለጡት ካንሰር ተጋላጭነታችው በዛው ልክ እየጨመረ ይሄዳል። በመሆኑም ሁሉም ሴቶች አመታዊ የጡት ካንሰርን የመለየት የማሞግራም (Mammogram) ምርመራ ማድረግ አለባቸው።

  • እድሜያቸው ከ 40 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች
  • ቢያንስ በአመት አንድ ጊዜ የካንሰር ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል
  • ምርመራውን ለማድረግ ትክክለኛው ጊዜ የወር አበባ ከታየ ከ 7 10ኛው ቀን በኋላ ነው።

ማሞግራም (Mammogram) ምንድን ነው?

ማሞግራም (Mammogram) ማለት የጡት ኤክስሬይ ምስል ማለት ነው። ማሞግራም በሚነሳበት ጊዜ ጡታችንን ማሽኑ ከላይ እና ከታች ጫን አድርጎ ይይዘዋል። የምርመራ ውጤቱን ለማረጋገጥና በተሻለ ለመመርመር ዶክተሩ ከማሞግራም በኋላ አልትራሳውንድ ምርመራ ሊያዝ ይችላል። ይሄ መደረጉ ምርመራውን ተቀራራቢና በጣም ውጤታማ ያደርገዋል። ስለዚህ እድሜያቸው ከ 20 አመት በላይ የሆኑ ሴቶች በወር አንድ ጊዜ በራሳቸው ጡታችውን በመነካካት መመርመር አለባቸው። እንዲሁም እድሜያችው ከ 40 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች ደግሞ በአመት አንድ ጊዜ ማሞግራም ምርመራ ለጡታቸውና ብብታችን አካባቢ የአልትራሳውንድ ምርመራ ማድረግ አለባችው።

ለበለጠ መረጃ :

የካንሰር ህክምና ክፍልን ያነጋግሩ

ስልክ ቁጥር: +662-734-0390 ext. 2200, 2204

  • Readers Rating
  • Rated 3 stars
    3 / 5 (2 )
  • Your Rating