ፕሮስቴት በፊኛ እና በወንድ ልጅ ብልት መካከል የሚገኝ እጢ ነው። ከሬክተም ፊት ለፊት ይገኛል እንዲሁም ሽንትን ከሰውነታችን ወደ ውጭ እንዲወገድ የሚያደርገው የሽንት ቧንቧ ደግሞ በመሃሉ አልፎ ይሄዳል። በዋናነት የወንድ ዘር ፈሳሽን (ስፐርምን) የሚመግብና የሚጠብቅ ፈሳሽ ያመርታል። ፕሮስቴት ካንሰር እጅግ በጣም በብዛት ወንዶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች አንዱ ነው።
በብዛት የፕሮስቴት ካንሰር በመጀመሪያ ከፕሮስቴት እጢ ላይ ተወስኖ የሚቆይና ከባድ ጉዳት በማያስከትል መልኩ ቀስ እያለ የሚያድግ ችግር ነው።አንዳንድ የፕሮስቴት ካንሰር አይነቶች ምንም አይነት ህክምና ላያስፈልጋቸው ይችላል ወይም ቀላል ህክምና ብቻ ሊያስፈልጋቸው ይችላል; ሌሎች ደግሞ በጣም ከባድ እና በፍጥነት የሚስፋፉ በመሆናቸው ልዩ ህክምና ይፈልጋሉ። ካንሰሩ የፕሮስቴት እጢው ላይ ብሻ ባለበት ሰአት (ማለትም ከመሰራጨቱ በፊት) በሽተኞች ውጤታማ የሆነ ህክምና ማግኘት ይችላሉ።
ምልክቶች – Prostate Cancer’s Symptoms
በዚህ ዙሪያ ያነጣጠሩ ምርምሮችን ከመስራት ባለፈ ፕሮስቴት ካንሰርን የሚያመጡ ምክንያቶች እስካሁን ምን እንደሆኑ ግልፅ አይደሉም።
በመጀመሪያ ጤናማ ሴሎች ሚውቴሽን ማድረግ እንዲሁም ጤናማ ያልሆኑ ይሆናሉ ይሄም በቀላሉ እንዲበለፅጉ፣ እንዲያድጉና በፍጥነት እንዲባዙ ያደርጋቸዋል። ጤናማ ያልሆኑ የሴሎች ስብስብ በአጠገቡ ወዳሉ ህብረህዋሳት የሚስፋፋና የሚወር ዕጢ ይፈጥራል።
የችግሩ መንስኤወች – Prostate Cancer’s Causes
እድሜ፡ እድሜ ሲጨምር የፕሮስቴት ካንሰር ተጋላጭነትም አብሮ ይጨምራል በተለይ ወንዶች እድሜያቸው ከ50 አመት በላይ ሲሆን ተጋላጭነታቸው ይጨምራል።
ዘር፡ ጥቁር ወንዶች ሌላ ዘር ካላቸው ወንዶች ይልቅ በፕሮስቴት ካንሰር የመጠቃት እድላቸው ከፍተኛ ነው። እንዲሁም በጣም አደገኛ ወይም የላቀ ሊሆን ይችላል።
ቤተሰብ ውስጥ ተይዞ የሚያውቅ ሰው ከነበረ: ቤተሰቡ በሚጋራቸው የካንሰር ዘረመሎች፣ የአመጋገብ ፣ የአኗኗር እና የከባቢ አየር ተፅዕኖ ተጣምረው ቤተሰባዊ የፕሮስቴት ካንሰር የመያዝ እድልን በትንሹ በመጨመር አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡ በተጨማሪም የቤተሰቡ አባላት ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ የምንለው አይነት ካንሰር ከ50 አመት በታች ባለው የወጣትነት እድሜያቸው ተይዘው ከነበረ በዘረመል ለውጥ (gene mutation) ምክንያት የመጣ ከትውልድ ወደ ትውልድ በዘር የሚተላለፍ የካንሰር አይነት ሊሆን ይችላል።
የዘረመል ለውጦች: ሌሎች ዘረመሎች HPC1, HPC2, HPCX, CAPB, ATM, FANCA, HOXB13, ጨምሮ የተሳሳተ የዘረመል አወቃቀር ያላቸውን ማስተካከል (mismatch repair genes) ለፕሮስቴት ካንሰር ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮችን ሊሸከሙ ይችላሉ፡፡
የኬሚካል ተጋላጭነት:የተወሰኑ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ለተለያዩ ኬሚካሎች ተጋላጭ የሆኑ ወንዶች ለፕሮስቴት ካንሰር ተጋላጭነታቸው ይጨምራል ለምሳሌ ኤጀንት ኦሬንጅ (agent orange) የተባለ ፀረ አረም፣ የግብርና ኬሚካሎች፣ እንዲሁም የተፈጥሮ ጋዝ ሲቃጠል ለሚፈጠሩ ጭሶች (combustion by-products) መጋለጥ ችግሮችን ያባብሳል።
ከልክ ያለፈ ውፍረት: ከልክ ያለፈ ውፍረት የፕሮስቴት ካንሰርን ጨምሮ ከሌሎች ብዙ የካንሰር በሽታወች ጋር ይያያዛል። ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የአመጋገብ ባህሪያችን ለካንሰር በሽታ ካለን ተጋላጭነት ጋር ግንኙነት አለው።
ደረጃዎች – Prostate Cancer Stages
የፕሮስቴት ካንሰር የህክምና እቅድ የሚታወቀው በተመረመርንበት እና ካንሰሩ ምን ያክል እንደተሰራጨ ባወቅንበት ሰዓት ነው። የስርጭት መጠኑን እና ፕሮስቴቱን ምን ያክል እንደጎዳው ለማወቅ ዶክተሩ ደረጃ ማውጣት (staging) የሚባል ዘዴ ይጠቀማል።
የግሊያሰን ሲስተም ከተወሰደው የህብረህዋስ ናሙና ውስጥ የሚገኙ በጣም የተለመዱ (የመጀመሪያ) እና ያልተልተለመዱ (ሁለተኛ) የህዋስ ቅጦች ከ1 እስከ አምስት በሆነ ደረጃ ይመድባቸዋል። የግሊሰን ውጤቱን ለመመስረት ይጣመራሉ የግሊሰን ውጤት ካንሰሩ ምን ያክል አደገኛ እንደሆነ ግልፅ መረጃ ይነግረናል። ዝቅተኛው የካንሰር ነጥብ 6 ነው ይሄ ማለት ዝቅተኛ ደረጃ ካንሰር ማለት ነው; 7 ደግሞ መካከለኛ ደረጃ ካንሰር ሲሆን; ከፍተኛ ደረጃ ካንሰር ደግሞ ነጥባቸው 8፣ 9 ወይም 10 ነው።
የፕሮስቴት ካንሰር ደረጃን ለማወቅ ዶክተሩ የTNM ሲስተምን ይጠቀማል። ሲስተሙ የዕጢውን ሦስት የተለያዩ የእድገትና የስርጭት ገፅታወችን ይጠቀማል፡
T= እጢ (tumour):ዋናው የፕሮስቴት ካንሰር ያለበት ቦታ መጠኑ ምን ያክል ነው?
N = ንፍፊት (nodes): ወደ ንፍፊቶች (ሊንፍ ኖድ) ተሰራጭቷል ወይ? ከሆነስ ምን ያክል?
M፡ መሰራጨት (metastasis): የፕሮስቴት ካንሰሩ ምን ያክል ርቀት ተስፋፍቷል?
ዶክተሩ ደረጃውን ለመመደብ የTNM ሲስተም ውጤትን፣ የግሊሰን ነጥብ እና የPSA መጠን ምርመራ ውጤትን አጣምሮ ይጠቀማል። ይህ ሲስተም የሮማን ቁጥሮችን ይጠቀማል እነሱም ከ I (ዝቅተኛ ደረጃ) እስከ IV(በጣም የዳበረ) ነው። ደረጃ ማውጣቱ ዶክተሩ የተሻለውን ህክምና እንዲመርጥ ይረዳዋል።
ህክምና – Prostate Cancer Treatment
ፕሮስቴት ካንሰር ለተገኘባቸው በሽተኞች የቬጂታኒ ሆስፒታል ካንሰር ማእከል አባላት ያሉትን የህክምና አማራጮች ከበሽተኛው ጋር ይወያያሉ። ዋና ዶክተርዎት ከእርስዎ ጋር በመሆን ረዥም ህይወት መኖር የሚያስችለዎትን፣ የጎንዮሽ ጉዳቱ የቀነሰውንና ፕሮስቴትዎን ሊያተርፍ የሚችል የህክምና እቅዶችን ያወጣል።
ስለ አራቱ ዋነ ዋና ለፕሮስቴት ካንሰር የሚሰጡ የህክምና አማራጮች ማብራሪያ፡ ቀዶ ጥገና፣ ጨረር፣ ኬሞቴራፒ፣ ሆርሞናል ህክምና ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል።
1) ቀዶ ጥገና (Surgery) – ፕሮስቴትን እና የተወሰኑ በአካባቢው ያሉ ጤናማ ህዋሳትን የማስወገድ ተግባር ሲሆን የሚከናወነውም በዩሮሎጂስት ሰርጅን አማካኝነት ነው። ዩሮሎጂስት ሰርጅን ማለት ካንሰርን በቀዶ ጥገና በማከም ልህቅና ያደረገ (specializes) ሃኪም ማለት ነው። የሚደረገው ቀዶ ጥገና እንደ በሽታው ደረጃ፣ የበሽተኛው አጠቃላይ የጤና ሁኔታ፣ እና ሌሎች የችግሩ መንስኤወች ይለያያል። ዋነኛ የህክምና አማራጩም ሙሉ ፕሮስቴቱን እና በአካባቢው ያሉ ንፍፊቶችን የማስወገድ ቀዶ ጥገና (radical prostatectomy) ሲሆን ክፍት ራዲካል ፕሮስቴክቶሚ እና ላፓራስኮፒክ (በሮቦት የታገዘ) ራዲካል ፕሮስቴክቶሚ በመባል ይታወቃል።
2) የጨረር ህክምና (Radiation) – ማለት የካንሰር ሴሎችን ለመግደል ionizing ጨረርን ወይም photons ስልታዊ የአጠቃቀም ዘዴ ነው። የሚሰራውም የካንሰር ህዋሱን ዘረመል(የካንሰር ሕዋስ የዘረመል ንድፍ) በመጉዳት ነው። በዋናነት ዒላማ የተደረጉት ሕዋሳት ሳያድጉ ወይም ራሳቸውን ሳይባዙ ይሞታሉ፡፡ ህክምናው የካንሰር በሽታን በጨረር ለማከም በሰለጠ የራዲየሽን ኦንኮሎጂስት (radiation oncologist) ዶክተር አማካኝነት ይሰጣል። በዋናነት የፕሮስቴት ካንሰርን ለማከም የምንጠቀምባቸው የጨረር ህክምና አይነቶች የሚከተሉት ናቸው፡
- ኤክስተርናል ቢም የጨረር ህክምና (External-beam radiation therapy)
- ብራኪ ህክምና (Brachytherapy)
- ኢንተንሲቲ ሞጁሌትድ የጨረር ህክምና (Intensity-modulated radiation therapy (IMRT))
- ፕሮቶን ህክምና (Proton therapy)
3) ኬሞቴራፒ (Chemotherapy) – ይህ ዘዴ የካንሰር ሴሎችን ለማጥፋት መድኃኒት መጠቀም ሲሆን፣ በብዛት የማደግ እና የመባዛት አቅማቸውን በማስቆም ይሆናል። ኬሞቴራፒ በዋናነት የሚሰጠው ካንሰርን በመድሃኒት ለማከም በሰለጠነ ሜዲካል ኦንኮሎጂስት ዶክተር አማካኝነት ነው። ሲስተሚክ ኬሞቴራፒ የሚባለው ወደ ካንሰሩ ህዋስ የሚደርሰው በደም ስር በኩል አድርጎ ነው። የኬሞቴራፒ አወሳሰድ በደም ሥር መርፌ በመጠቀም በሚተከል የደም ሥር (IV) ቱቦ አማካኝነት ነው።
4) የሆርሞን ህክምና (Hormone Therapy) – ቴስቴስትሮን ለፕሮስቴት ካንሰር ሕዋስ እድገት ዋና ነዳጅ ሆኖ የሚያገለግል በመሆኑ ሕክምና ሲደረግም ዋነኛ ዒላማ ይሆናል። የመጀመሪያ ደረጃ የሆርሞን ህክምና (የአንድሮጅን እጦት ህክምና (Androgen Deprivation Therapy) [ADT] በመባል የሚታወቀው) ከፍተኛ ደረጃ ላይ ለደረሰና ለተሰራጨ የፕሮስቴት ካንሰር የሚሰጥ ደረጃውን የጠበቀ ህክምና አካል ነው። ADT ቴስቶስትሮን በፕሮስቴት ካንሰር ላይ አስተዋፅኦ እንዳይኖረው እንዲሁም / ወይም ከጀመሪያው እንዳይመረቱ በቀጥታ ለመዝጋት ታቅዶ የተሰራ ነው። የፕሮስቴት ካንሰርን እድገት በማዘግየት በኩል በጣም ውጤታማ የሚባል ነው። የADT ህክምና መጥፎ ጎኑ ከሁሉም በሽተኛወች ላይ በሚባል መልኩ የጎንዮሽ ጉዳት ያስከትላል; የአጥንት ጥንካሬን ከማሳጣት ጀምሮ፣ ያልታሰበ የላይኛው የሰውነት ሙቀት መከሰት፣ የባህሪ መቀያየር፣ ስንፈተ ወሲብ እና የሰውነት ክብደት መጨመር ድረስ ይሰፋል።
የሚያስከትላቸው ችግሮች – Complications of Prostate Cancer
መሰራጨት፡ የፕሮስቴት ካንሰር በአካባቢው ወዳለ የሰውነት ክፍል ወይም አጥንት ሊሰራጭ ይችላል። አንዴ ይሄ ከተፈጠረ በሽታው አሁንም ሊታከምና መቆጣጠ ሊቻል ይችላል ነገር ግን ሙሉ በሙሉ መፈወስ አይቻልም።
ሽንት አለመቆጣጠር፡ የፕሮስቴት ካንሰርም ሆነ ህክምቻው የሽንት ስርዓቱ ላይ ችግር ያስከትላሉ። ህክምናው እንደበሽታው ክብደትና አይነት ይለያያል ነገር ግን በዋናነት መድሃኒቶችን፣ የሽንት መሽኛ ካቴተር (catheters)፣ እና ቀዶ ጥገና በብዛት ይካተታሉ።
ስንፈተ ወሲብ፡ ከካንሰሩ ከራሱ ወይም ከሱ ጋር ተያይዘው በሚሰጡ ህክምናወች (ቀዶ ጥገና፣ ጨረር፣ የሆርሞን ህክምና) ምክንያት ይመጣል። መድሃኒቶች፣ የቫኪዩም መሣሪያዎች እና የቀዶ ጥገና ህክምና መደበኛ የህክምና መንገዶቹ ናቸው፡፡ ለተሟላ ሙሉ የላብራቶሪ፣ የምርመራ፣ የህክምና እና የማገገሚያ ህክምና ቬጂታኒ ሆስፒታል የሚገኘውን የካንሰር ክፍል ይጎብኙ። ባንኮክ ውስጥ የተሻለ የፕሮስቴት ካንሰር ህክምና ለእርስዎ ለማቅረብ እጅግ ዘመናዊ የሆኑ መሳሪያወች እና ልምድ ያላቸው የህክምና ባለሙያወች ቡድን አሟልተን እንገኛለን፡፡
- Readers Rating
- Rated 3.5 stars
3.5 / 5 (Reviewers) - Very Good
- Your Rating