ከ98% በላይ የሚሆኑ ልክ ያልሆነ የልብ ምት(Arrhythmia) ያለባቸው በሽተኞች በኤሌክትሮፊዚዮሎጂ ጥናት (EP study) እና ራዲዮፍሪኩየንሲ አብሌሽን (RFA) መታከም ይችላሉ። - Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand.

የጤና መረጃዎች

ከ98% በላይ የሚሆኑ ልክ ያልሆነ የልብ ምት(Arrhythmia) ያለባቸው በሽተኞች በኤሌክትሮፊዚዮሎጂ ጥናት (EP study) እና ራዲዮፍሪኩየንሲ አብሌሽን (RFA) መታከም ይችላሉ።

Share:

ልክ ያልሆነ የልብ ምት (Arrhythmia) ችግር ላለባቸው ሰዎች ብዙ አይነት የህክምና አማራጮች አሉ; እንደ በሽታው አይነትና ክብደት የሚሰጡት ህክምናወች ይለያያሉ።በጣም ውጤታማ ከሚባሉት ልክ ያልሆነ የልብ ምት (Arrhythmia) የህክምና አማራጮች አንዱ ራዲዮፍሪኩዌንሲ አብሌሽን ወይም በአጭሩ RFA ተብሎ የሚታወቀው ነው። RFA ቀዶ ጥገና የሌለው፣ ምንም አይነት የህክምና መሳሪያ ወደ ሰውነት ማስገባት የማያስፈልገው (minimally invasive procedure) የህክምና አይነት ሲሆን ትክክለኛ ያልሆን የኤሌክትሪካል ሲግናሎች የሚነሱባቸው ቦታ ልብ ውስጥ ሲገኝ ወዲያውኑ እንደተገኙ የራዲዮፍሪኩዌንሲ ሀይልን በመጠቀም ጤናማ ያልሆኑ ሴሎችን ለማጥፋት የምንጠቀምበት የህክምና ሂደት ነው።

ከ98% በላይ የሚሆኑ ልክ ያልሆነ የልብ ምት (Arrthythmia) ያለባቸው በሽተኞች በኤሌክትሮፊዚዮሎጂ ጥናት (EP study) እና ራዲዮፍሪኩየሲ አብሌሽን (RFA) መታከም ይችላሉ እንዲሁም ቀሪ ህይወታቸውን መድሃኒት መውሰድ አያስፈልጋቸውም።

ልክ ያልሆነ የልብ ምትን (Arrthythmia) ለመለየት ሁለት አይነት ቴክኖሎጂዎች አሉ፣ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፥

  • የሁለት ዳይሜንሽን ኤሌክትሮ አናቶሚካል ማፒንግ ሲስተም (2D electro anatomical mapping system) በኤሌክትሮፊዚዮሎጂ ጥናት (EP study) ውስጥ ከልብ የሚመጣውን የኤሌክትሪካል ሲግናል ለመመርመርና ለማረጋገጥ እንዲሁም ልክ ያልሆነ የኤሌክትሪካል ሲግናል ከየት እንደሚመጣ ለመለየት ይረዳናል። ልክ ያልሆነው የኤሌክትሪካል ሲግናል ከተለየ በኋላ የልብ ስፔሻሊስቱ ወዲያውኑ ከኤሌክትሮፊዚዮሎጂ ጥናቱ (EP study) እንደተጠናቀቀ የራዲዮፍሪኩዌንሲ አብሌሽን ህክምና ያከናውናል።
  • ሶስት ይሜንሽን ኤሌክትሮ አናቶሚካል ማፒንግ ሲስተም 3D electro anatomical mapping system) ይሄምበኤሌክትሮፊዚዮሎጂ ጥናት (EP study) ውስጥ ከልብ የሚመጣን ልክ ያልሆነ የኤሌክትሪካል ሲግናል ለመለየት ያገለግላል፣ ነገር ግን ይሄ መንገድ የልብ ስፔሽያሊስቱ ውጤቱን በሶስት ዳይሜንሽን ምስል (3D images) በዚያውኑ ሰዓት (real-time) እየተከናወነ ያለውን ነገር ማየት ይችላል። ችግሩ ከተለየ በኋላ የልብ ስፔሻሊስቱ የራዲዮፍሪኩዌንሲ አብሌሽን (RFA) ህክምና ያከናውናል። በዋናነት የልብ ስፔሻሊስቱ እንደዚህ አይነት ቴክኖሎጂወቺን የሚጠከመው ከባድና ውስብስብ ጉዳዮች ሲያጋጥሙት ነው ለምሳሌ፥
    • ኤትሪያል ታኪካርዲያ (Atrial tachycardia)
    • ኤትሪያል ፋይብሪሌሽን (Atrial fibrillation)
    • ቬንትሪኩላር ታኪካርዲያ (Ventricular tachycardia)
    • ሱፐርቬንትሪኩላር ታኪካርዲያ (Supraventricular tachycardia)

ለበለጠ መረጃ የልብ ምርመራ ክፍላችን ያነጋግሩ 5ኛ ፍሎር; ቬጂታኒ ሆስፒታል ወይም በስልክ ቁጥር +66(0)2-734-0000 ext. 5300 ይደውሉ።

  • Readers Rating
  • Rated 5 stars
    5 / 5 (2 )
  • Your Rating