“ካንሰር – Cancer” በጣም አደገኛ የሆነ እና ከምናስበው በላይ እየጨመረ የመጣ በሽታ ነው። እንደ የአለም የጤና ድርጅት አዲሱ የአለማቀፍ የካንሰር መረጃ መሰረት የካንሰር ተጠቂዎች ቁጥር ወደ 19.3 ሚሊየን የጨመረ ሲሆን 10 ሚሊየን የሚሆን የካንሰር ሞት ደግሞ በ2020 ተመዝግቧል። ይህም ማለት በአለማቀፍ ደረጃ ከ5 ሰዎች በ1 ሰው ላይ በህይወት ዘመኑ ካንሰር የመያዝ እድል ያጋጥመዋል ማለት ነው።
ይሁን እንጂ የካንሰር ህመም መከላከል የምንችለውና እና ታክሞ መዳን የሚችል በሽታ ነው።
በዚህ ዘመን ውጤታማ የሆኑ ክትባቶች ምሳሌ የሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ (HPV) እና የሄፓታይተስ ቢ (Hepatitis B) ክትባቶች የማህፀን በር ካንሰርን (Cervical cancer) እና የጉበት ካንሰርን (Liver cancer) ለመከላከል የሚያገለግላሉ ውጤታማ ክትባቶች ናቸው። የካንሰር ምርመራ ዘዴወች በጣም ተሻሻለውና ውጤታማ ሆነው የተሰሩ በመሆናቸው ማንኛውም ጤናማ ያልሆነን ወይም ካንሰርን ገና በመጀመርያው ደረጃ ላይ እያለ መለየት ያስችላሉ።
ብዙ አይነት የካንሰር ህክምና አማራጮች ያሉ ሲሆን (Cancer Treatment) ለምሳሌ ታርጌትድ ቴራፒ(Targeted Therapy) ኢሚውኖ ቴራፒ (Immunotherapy) የሚባሉት በጣም ውጤታማ ሆነው የተሰሩ ነገር ግን የጎንዮሽ ጉዳታቸውም ዝቅተኛ የሆኑ የህክምና አማራጮች ናቸው። ይሁን እንጂ የካንሰር የህክምና እንደ ካንሰሩ አይነትና ደረጃ የሚለያይ ይሆናል። በዚህ አለማቀፍ የካንሰር ቀን ቬጂታኒ ሆስፒታል ሁሉም ሰው ስለ ካንሰር ግንዛቤ እንዲኖረው እንዲሁም ስለሚያስከትላቸው ችግሮች እና ስለህክምናው እንዲረዳ ይፈልጋል። ምክንያቱም ካንሰር በጣም አደገኛ ከሚባሉት በሽታዎች አንደኛውና ከምናስበው በላይ በጣም እየጨመረ የመጣ በሽታ በመሆኑ ነው።
- Readers Rating
- Rated 4.8 stars
4.8 / 5 (Reviewers) - Spectacular
- Your Rating