ሥር የሰደደ የአፍንጫ መዘጋት (Chronic Nasal Congestion)

የጤና መረጃዎች

ሥር የሰደደ የአፍንጫ መዘጋት (Chronic Nasal Congestion) ችግር መዳን ይችላል

Share:

ሥር የሰደደ የአፍንጫ መዘጋት (Chronic Nasal Congestion) ታካሚው ጥሩ ሕይወት እንዳይኖረው ተፅእኖ ያሳድራል፡፡ ይህ ችግር በጥናት እንዲሁም በሥራ ወቅት የሰዎችን ትኩረት ያስተጓጉላል፡፡ መደበኛ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን ፈታኝ ሊያደርግብንና ቀኑን ሙሉ በድካም ስሜት ውስጥ እንድናልፍ ወደሚያደርግ የእንቅልፍ እጦት ችግር ሊያመራ ይችላል። የአፍንጫ መዘጋትን ከሚያስከትሉት ምክንያቶች መካከል አንደኛው የአፍንጫ ውስጠኛው ሽፋን (Turbinate) ወይም የአፍንጫ septum ላይ ብግነት (inflamation) ሲከሰት ነው፡፡ ይህ ችግር ያለበት በሽተኛ የማስነጠስ፣ የአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት፣ ራስ ምታት እንዲሁም የመተንፈስ ችግር እና መሰል ምልክቶች አሏቸው፡፡

ሥር ለሰደደ የአፍንጫ መዘጋት የሚደረግ ሕክምና

የአንገት በላይ (ENT) ባለሙያ ወይም otolaryngologist በመጀመሪያ የአፍንጫ መዘጋት መንስኤው ምን እንደሆነ ለማዎቅ አካላዊ ምርመራ ያካሂዳል፣ ከዚያም እንደ በሽታው መንሰኤ የሚከተሉትን ዘዴዎች በመጠቀም ለበሽተኛው ተገቢውን ህክምና ይሰጣል;

  • የአፍንጫ የውስጠኛው ግድግዳ (rhinitis) አለርጂ ላለባቸው በሽተኞች ያለባቸውን የሕመም ምልክቶች ለመቆጣጠር የአለርጂ መድኃኒቶች ይታዘዛሉ፡፡
  • ከባድ የሆነ የአፍንጫ ውስጠኛው ግድግዳ ቅርፅ መዛባት ለገጠማቸው ታካሚዎች ደግሞ የአፍንጫ septum ማስተካከያ ቀዶ ጥገናን እንዲሰራላቸው ይመከራል፣ ወይም የአፍንጫ ውስጠኛው ክፍል ብግነት ላጋጠማቸው በሽተኞች ፀረ-ብግነት መድኃኒቶች ይታዘዛሉ፡፡ ታካሚው ለተሰጡት መድኃኒቶቹ ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ ወይም አሁንም ያበጠ turbinate ያለው ከሆነ ሐኪሙ የሬዲዮ ፍሪኩዌንሲ (RF) ሕክምናን እንዲያደርግ ይመክራል፡፡

ያበጠ ቱርቢኔት ለመቀነስ (Turbinate Reduction) የሚደረግ የሬዲዮ ፍሪኩዌንሲ (Radiofrequency – RF) ሕክምና

በሬዲዮ ፍሪኩዌንሲ (Radiofrequency – RF) ህክምና ወቅት የጉሮሮ እና ጆሮ (otolaryngologist) ባለሙያው ልዩ የሆነ መርፌ ወደ turbinate ውስጥ ያስገባል ከዛም ራዲዮ ፍሪኩዊንሲው ወደ ሙቀት ሀይል ተቀይሮ የturbinate እብጠቱን ለመቀነስ እንዲረዳ እንዲሁም በአፍንጫ ውስጥ የተሻሻለ የአየር ፍሰት እንዲኖር ሙቀቱ ወደ ህብረ ህዋሱ (tissue) እንዲተላለፍ ይደረጋል፡፡ በተጨማሪም የሬዲዮ ፍሪኩዌንሲ ሕክምና የሚያሳክክ ስሜትን፣ የአፍንጫ ፍሳሽ መብዛትን እንዲሁም ጉሮሮ ላይ የሚኖር አክታን መቀነስ ይችላል፡፡ ምናልባት ታካሚው በturbinate እብጠት ምክንያት የአፍንጫ መደፈን እንደገና ከገጠመው ከበፊቱ ተመሳሳይ የሆነ የህክምና ዘዴ አገልግሎት ላይ ይውላል፡፡

For more information, contact

ENT Center, Vejthani Hospital
Call 02-7340000 or Ext. 3400
English Hotline: (+66)8-522 38888

  • Readers Rating
  • Rated 3 stars
    3 / 5 (6 )
  • Your Rating




Related Posts