ቀጥ ያለ (ጠፍጣፋ) የውስጥ እግር (Flat Feet) ያላቸው ሰዎች መደበኛ የእግር ጫማ ካላቸው በበለጠ ለጉዳት የመጋለጥ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ቀጥ ያለ የውስጥ እግር ያላቸው ሰዎች ብዙውን ጊዜ ከጉልበት በታች ያለው የእግራቸው ረዥም አጥንት የውስጠኛ ጠርዝ ላይ የህመም ስሜት ይኖራቸዋል በተጨማሪም በጉልበታቸው የፊተኛው ክፍል ላይ፣ የጉልበት እፊያ የሚባለው አካባቢ (የጉልበት እፊያና የጭን አጥንት ህመም ሲንድሮም (Patellofemoral Pain Syndrome)) ላይ ህመም አላቸው ፣ እነዚህ ሩጫ ያለባቸው ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በሚሳተፉ ሰዎች የሚከሰቱ የተለመዱ ምልክቶች ናቸው፡፡
ለዚህም ዋነኛ ምክንያቱ ሙሉው የእግር ጫማ ክፍል ሙሉ በሙሉ ወይም በጣም ተቀራራቢ በሚባል መልኩ ከመሬቱ ጋር ስለሚገናኝ ይሄን ተከትሎም በውስጥ እግር እና በቁርጭምጭሚት ላይ ከፍተኛ ጫና ስለሚፈጥር ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ጠፍጣፋ የውስጥ እግር ያላቸው ሰዎች በውስጥ እግራቸው እና ከጉልበት በታች ባለው ትልቁ አጥንታቸው ላይ ለህመም የመጋለጥ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡ በተጨማሪም ጠፍጣፋ እግር ያላቸው ሰዎች በጉልበታቸው ላይም ከፍተኛ ጫና ያሳድራል ይሄም በጉልበታቸው እና በጀርባዎቻቸው ላይ ለሚሰማቸው ህመም አንዱ መንስኤ ነው፡፡
ሐኪም ማየት የሚያስፈልገው መቼ ነው?
በዋናነት ጠፍጣፋ የውስጥ እግሮች አብዛኛውን ጊዜ ህመም የላቸውም ነገር ግን በቁርጭምጭሚት እና ከጉልበት በታች ባለው አጥንት በተለምዶ የእግር አገዳ የምንለው ላይ በሙሉ በውስጠኛው ጠርዝ በኩል ህመም ካለብዎት እና በጣም እየተባባሰ ከሆነ፣ በተቻለ ፍጥነት ህክምና ማግኘት አለብዎት።
ምልክቶችን ችላ ካሉ በጡንቻዎች እና በአጥንቶች ላይ የበለጠ ጉዳት ያስከትላል፣ ለተወሰነ ጊዜ ሩጫዎን እና የሚወዷቸው እንቅስቃሴዎች እንዲያቆሙ ያደርግዎታል፡፡
ለበለጠ መረጃ ቬጅታኒ ሆስፒታል የአጥንት ህክምና ማዕከላችን 3ኛ ፎቅ ላይ ያገኙናል በስልክ ቁጥር +66 (0) 2-734-0000 ext.2298 ወይም +66 (0) 90-907-2560 (የኢትዮጵያ መስመር) ይደውሉ፡፡
- Readers Rating
- Rated 4.8 stars
4.8 / 5 (Reviewers) - Spectacular
- Your Rating