ብዙ ሰዎች ምንም እንኳን በርካታ ህክምናዎችን ቢያደርጉም በከባድ ህመም ከመሰቃየት ሲገላገሉ አይታዩም ህመማቸው አሁንም ድረስ የሚኖርና ክብደቱም እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ይህ ችግር የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቻቸውን፣ ሥራዎቻቸውን፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎቻቸውን እና የአእምሮ ጤንነታቸው ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡
Red Cord Suspension (የነርቭና ጡንቻዎች ማነቃቂያ ዘዴ) ህመምን ለመቆጣጠር (Pain Management) አንደኛው እና ውጤታማው የሕክምና ዘዴ ነው፡፡ Red Cord Suspension እና የነርቭና ጡንቻዎች ማነቃቂያ ዘዴዎች ማንኛውም የአካል ክፍል ላይ ያለ ህመምን ኢላማ ተደርገው ሊሰጡና እፎይታን ሊያስገኙ የሚችሉ ዘዴዎች ናቸው፡፡
በመሠረታዊነት ሰውነታችን ለህመም የሚሰጠው መደበኛ ምላሽ ይኖረዋል፡፡ የነርቭ ሥርዓታችን አንዳንድ ጡንቻዎችን ተግባራቸውን ለማስቆም ወይም ለማወክ መልዕክት ይልካል በዚህም ምክንያት የጡንቻዎች ተግባር ያልተመጣጠነ እንዲሆን ያደርጋል። እንዲሁም ከመጠን በላይ እንዲሰራ ወይም እንቅስቃሴ-አልባ ሊያደርጋቸው ይችላል። በመገጣጠሚያዎች እና በዋነኛ ጡንቻዎች አካባቢ የሚከሰት ያልተመጣጠነ የጡንቻዎች ተግባር ወደ መገጣጠሚያ ጉዳት እንዲሁም የመገጣጠሚያዎች ፣ ጅማቶች እና የአከርካሪ አጥንቶች ማርጀትን ሊያስከትል ይችላል። የከፉ ሁኔታዎች ሲኖሩ የበለጠ ህመም ያስከትላል፡፡
ከነርቭ እና ጡንቻዎች ማነቃቂያ ዘዴ ጋር በማቀናጀት የምንጠቀመው Red Cord Suspension በያንዳንዱ ደረጃ የሚገኙ ነርቮችና ጡንቻዎቻችን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያነቃቃ እንቅስቃሴ በማሰራት የጡንቻዎችን መደበኛ ተግባር ለመመለስ ታቅዶ የሚሰጥ ህክምና ሲሆን ህመምተኛው ህመሙን ከምንጩ በአጭር ጊዜ ለማስታገስ የሚያስችለው ህክምና ነው፡፡ በሕክምናው ወቅት ምንም ዓይነት ህመም ወይም ጉዳት ካለማስከትሉ በተጨማሪ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሁኔታዎች ላለባቸው ታካሚዎች ተስማሚ ነው:-
- በኦፊስ ሲንድረም ምክንያት ለተከሰተ ህመም
- በህብለ ሰረሰር ማርጀት (spondylosis) ምክንያት ለሚመጣ ህመም
- በስፖርታዊ ጉዳት ምክንያት ለሚከሰት ፅኑ ጉዳት
- ትከሻ ላይ እጃችን እንዲሽከረከር የሚያግዙ አጥንትን ከአጥንት የሚገናኙ ጅማቶች (tendon) ላይ በሚከሰት ብግነት ወይም በrotator cuff syndrome ለሚከሰት የትከሻ ህመም
- ለድህረ-ህብለ ሰረሰር ቀዶ ጥገና ወይም ለጉልበት ጅማት ጉዳት የሚደረግ ቀዶ ጥገና
በመሆኑም በህመም ወይም በፅኑ የአካል ጉዳት እየተሠቃዩ ከሆነ ችግሩ እየከፋ ከመሄዱ በፊት ህመምዎን ለማስታገስ የሚያግዙ ትክክለኛ ምርመራዎችን ለማድረግና የተሻለ የሚስማማዎትን ህክምና ለማግኘት በተቻለ ፍጥነት የህመም ስፔሻሊስት ሃኪም (Pain Management Specialist) ጋር እንዲሄዱ እንመክራለን።
- Readers Rating
- Rated 4.8 stars
4.8 / 5 (Reviewers) - Spectacular
- Your Rating