የፊንጢጣ ኪንታሮት (Hemorrhoid) አለብዎት? ካለብዎትስ ምን ያህል ከባድ ነው?

የጤና መረጃዎች

የፊንጢጣ ኪንታሮት (Hemorrhoid) አለብዎት? ካለብዎትስ ምን ያህል ከባድ ነው?

Share:

ውስጣዊ የፊንጢጣ ኪንታሮት (ሄሞሮይድ – Internal Hemorrhoid) እንደ ክብደት ደረጃቸው በ4 የተለያዩ ደረጃዎች ይመደባሉ።

የመጀመሪያደረጃ: ኪንታሮቱ ወይም ያበጠው የደም ስር በፊንጢጣ ውስጥ ወይም በታችኛው የሬክተም ክፍል ላይ ያድጋል። በዚህ ደረጃ ላይ ለሚገኝ ሄሞሮይድ ዋነኛ የህክምና አማራጩ መድሃኒት ወይም በተጎዳው ክፍል ላይ የሚሰጥ መርፌ ነው።

ሁለተኛደረጃ: የፊንጢጣ ኪንታሮት (Hemorrhoids) ሰገራ በሚወገድበት ወቅት በፊንጢጣ በኩል ወደ ውጭ ይወጣል ነገር ግን ተጠቅመን ስንጨርስ በራሱ ተመልሶ ይገባል። በዚህ ደረጃ ላይ ለሚገኝ የፊንጢጣ ኪንታሮት ዋነኛ ህክምና አማራጭ የኪንታሮቱ መነሻ ላይ በራበር ባንድ በማሰር ደም ወደ ሄሞሮይዱ እንዳይደርስ የማድረግ (rubber band ligation) ህክምና ነው።

ሶስተኛደረጃ: የፊንጢጣ ኪንታሮቱ (Hemorrhoids) ሰገራ በሚወገድበት ወቅት በፊንጢጣ በኩል ወደ ውጭ ይወጣል ነገር ግን ተጠቅመን ስንጨርስ በራሱ ተመልሶ አይገባም። ይሁን እንጂ በእጣት ተገፍቶ ይገባል። በዚህ ደረጃ ላይ ለሚገኝ የፊንጢጣ ኪንታሮት ዋነኛ ህክምናው የሌዘር ቀዶ ጥገና (Laser-Hemorrhoidectomy) ህክምና ነው።

አራተኛደረጃ: የፊንጢጣ ኪንታሮት (Hemorrhoids) ሰገራ በሚወገድበት ወቅት በፊንጢጣ በኩል ወደ ውጭ ይወጣል እንዲሁም ተጠቅመን ስንጨርስ በእጣት ተገፍቶ ወደ ውስጥ ተመልሶ አይገባም። ከዚህ ደረጃ ላይ የደረሰ የፊንጢጣ ኪንታሮት ከባድ ህመም ያለው እና አደገኛ ነው። በመሆኑም በተቻለ መጠን ሄሞሮይድ የተከሰተበት የደም ስር ውስጥ የደም መርጋት ተከስቶ የደም ዝውውሩን የመዝጋት ችግር (Thrombosed Hemorrhoids) ከመቀየሩ በፊት ሃኪም ማማከር አስፈላጊ ነው። በዚህ ደረጃ ላይ ለሚገኝ የፊንጢጣ ኪንታሮት ዋነኛ ህክምናው የሌዘር ቀዶ ጥገና (Laser-Hemorrhoidectomy) ህክምና ነው።

በሌዘርቀዶጥገና (Laser-Hemorrhoidectomy) ህክምናታካሚውበሰውነቱላይእጅግአነስተኛየሆነመቀደድያጋጥመዋል፣ዝቅተኛህመምይኖረ ዋልእንዲሁምበፍጥነትያገግማል።

  • Readers Rating
  • Rated 2.7 stars
    2.7 / 5 (42 )
  • Your Rating