የዘመናችን የህክምና ቴክኖሎጂዎች ለእግር እና ቁርጭምጭሚት የሚደረጉ ቀዶ ጥገናዎች ህመምተኞች ላይ እጅግ አነስተኛ የሰውነት መቀደድ፣ ዝቅተኛ ህመም እና ፈጣን የማገገም አቅም እንዲኖራቸው የሚያስችለውን የኢንዶስኮፒ እና የአርትሮስኮፒን እንደሚጠቀሙ ሆነው እየተሰሩ ነው።
አነስተኛ መቀመደድ ብቻ በሚያስፈልገው ቀዶ ጥገና (Minimally Invasive Surgery) ሊታከሙ የሚችሉ የእግር ጫማ እና የቁርጭምጭሚት ችግሮች
- ተረከዝን ከባት የሚያገናኘው ጅማት መበጠስ (Achilles Tendon Rupture)
- ቁርጭምጭሚት አካባቢ ያለው ህብረ ህዋስ ጉዳት (Soft Tissue Ankle Injury)
- በጫማችንና ሽምብራ አጥንት መካከል ባለው የመገጣጠሚያ ለስላሳ አጥንት ላይ የሚከሰት ጉዳት (Fibrocartilage)
- በእግር ጫማ እና ቁርጭምጭሚት መገጣጠሚያዎች ላይ የማርጀት በሽታ
- ተረከዛችን ከእግራችን ጣቶች ጋር የሚያያይዘው ጅማት ላይ በሚከሰት ብግነት ምክንያት የሚመጣ ሥር የሰደደ የተረከዝ ህመም (Chronic Plantar Fasciitis)
- ተረከዝን ከባታችን የሚያያይዘው ጅማት ላይ የሚከሰት ጉዳት (Achilles Tendinitis)
አነስተኛ መቀመደድ ብቻ የሚያስፈልገው ቀዶ ጥገና አሰራር ሂደት (Minimally Invasive Surgery for Foot and Ankle)
በቀዶ ጥገና ሂደቱ ወቅት የቀዶ ጥገና ሐኪሙ 8 ሚሜ የሚሆን ቆዳችን ክፍል ላይ ከቀደደ በኋላ ቀጭን ተጣጣፊ 4.0 ሚሜ ወይም 2.7 ሚ.ሜ. የፋይበር ኦፕቲክ ካሜራ (ኢንዶስኮፒ ወይም አርተሮስኮፒ) እና ሌሎች መሳሪያዎች የተጎዳውን አካባቢ ምርመራ እና ሕክምናውን ለማካሄድ በተቀደደው ቦታ በኩል ይገባሉ፡፡ በሰአቱ የሚከናወነውን ተግባር በቀጥታ የኮምፒውተር ስክሪኑ ላይ ይታያል። በተጨማሪም የቀዶ ጥገና ሐኪሙ አጠቃላይ የቀዶ ጥገና ሂደቱን ቪዲዮ መቅዳት ይችላል፡፡
አነስተኛ መቀመደድ ብቻ የሚያስፈልገው ቀዶ ጥገና ጥቅሞች (The Advantages of Minimally Invasive Surgery for Foot and Ankle)
Minimally Invasive Surgery ያደረጉ ህሙማኖች ክፍት ቀዶ ጥገና ካደረጉት ጋር ሲነፃፀሩ በአጥንታቸው እና በህብረ ህዋስ (tissue) ላይ የሚደርሰው ጉዳት አነስተኛ በመሆኑ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን ማከናወን ጊዜ አይወስድባቸውም፣ በዚህም ምክንያት ህመምተኞቹ ፈጣን የማገገሚያ እና ለተጎዳው አካል የሚለበሰው ድጋፍ ለአጭር ጊዜ ብቻ እንዲሆን ያስችላቸዋል፡፡
Minimally Invasive surgery ከቀዶ ጥገናው በኋላ በተለይም የስኳር በሽታ ላለባቸው ህመምተኞች የኢንፌክሽን ስጋትን ይቀንሳል፡፡ በተጨማሪም ህመምተኞቹ የሆስፒታል ቆይታ ጊዜያቸው እንዲቀንስ በማድረግ የህክምና ወጪዎቻቸውን እንዲቆጥቡ ያስችላቸዋል፡፡
- Readers Rating
- Rated 5 stars
5 / 5 (Reviewers) - Spectacular
- Your Rating