ከአፍንጫ ጀርባ ወደ አንገት መውረጃ ባለው የሰውነት ክፍል ላይ የሚከሰት ካንሰር (Nasopharyngeal Cancer) በምን እንደሚከሰት ትክክለኛ ምክንያቱ አልታወቀም። ይሁን እንጂ ለበሽታው አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የተለያዩ ምክንያቶች እንዳሉ ይታመናል።
- Epstein-Barr Virus (EBV)፦ በምራቅ የሚተላለፍ በመሆኑ የመሳሳም በሽታ በመባል የሚታወቅ ሲሆን mononucleosis የተባለ ኢንፌክሽን የሚያስከትል ቫይረስ ነው። ሄርፕስ ቫይረስ ጋር ተመሳሳይ ምድብ ላይ ይገኛሉ። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከአፍንጫ ጀርባ ወደ አንገት መውረጃ ባለው የሰውነት ክፍል ላይ የሚከሰት ካንሰር (Nasopharyngeal Cance) ያለባቸው ታካሚዎች ከአብዛኛው ሰው በበለጠ ለ mononucleosis በሽታ ያላቸው የመከላከል አቅም (immunity) ከፍተኛ ነው።
- Nitrosamine፦ በቆዳ፣ በጎማ እና በብረታ ብረት ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም በተቀነባበሩ እና በተብላሉ ምግቦች ውስጥ በተጨማሪም በተጠበሰ ስጋ ላይ በስፋት ተነካክቶ የሚገኝ ኬሚካል ነው።
- ጭስና አቧራ፦ የእንጨት ጭስም ሆነ፣ የሲጋራ ጭስ ወይም አቧራ ሊሆን ይችላል። ለእነዚህ ጭሶች ረዘም ላለ ጊዜ መጋለጥ ለ ከአፍንጫ ጀርባ ወደ አንገት መውረጃ ባለው የሰውነት ክፍል ላይ የሚከሰት ካንሰር (Nasopharyngeal Cance) ተጋላጭነት አስተዋጽኦ ሊያደርግ ይችላል።
- ጥሩ ያልሆነ የአፍ ጤንነት፦ መጥፎ የአፍ ንፅህና አያያዝ ወይም የአፍንጫ የውስጠኛው ክፍል መቆጣት(ሥር የሰደደ የአፍንጫ ውስጥ መቆጣት (chonic rhinitis) ወደ ከአፍንጫ ጀርባ ወደ አንገት መውረጃ ባለው የሰውነት ክፍል ላይ የሚከሰት ካንሰር (Nasopharyngeal Cance) ሊያመራ ይችላል።
እነዚህን ለችግሩ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ምክንያቶች ማስወገድ ወደ ከአፍንጫ ጀርባ ወደ አንገት መውረጃ ባለው የሰውነት ክፍል ላይ የሚከሰት ካንሰር (Nasopharyngeal Cance) ሊያመሩ የሚችሉ ችግሮችን ይቀንሳል። በመጀመሪያ ደረጃ ላይ እያለ ምርመራ ከተደረገለት እና ህክምና ካገኘ በሽታው ሙሉ በሙሉ ሊድን ይችላል። ሐኪሙ የራዲዮቴራፒ ሕክምና ን በብቸኝነት ወይም ከኬሞቴራፒ ጋር በማጣመር ሊያዝልን ይችላል። የሕክምናው ሂደት የሚወሰነው በካንሰሩ ደረጃ እና በእያንዳንዱ በሽተኛ የጤና ሁኔታ ላይ ተመስርቶ ነው።
- Readers Rating
- Rated 3.5 stars
3.5 / 5 (Reviewers) - Very Good
- Your Rating