የቬጂታኒ Diabetic Foot Ulcer እና ቁስል ህክምና ማዕከልን ምን ተመራጭ ያደርገዋል?

የጤና መረጃዎች

የቬጂታኒ Diabetic Foot Ulcer እና ቁስል ህክምና ማዕከልን ምን ተመራጭ ያደርገዋል?

Share:

ቬጅታኒ ሆስፒታል በአጥንት ክፍል በሚሰጠው ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎቶች ምክንያት “የአጥንት ንጉሥ” በመባል ይታወቃል። ነገር ግን የቬጂታኒ ሆስፒታል የሚሰጠው ቁልፍ አገልግሎት ይህ ብቻ አይደለም ይልቁንም ከብዙዎች መካከል አንዱ ብቻ ነው። ሁላችንም እንደምናውቀው “የስኳር በሽታ” በዓለም አቀፍ ደረጃ የጨመረ እና አሁንም እየጨመረ ያለ በሽታ ነው። በችግሩ ለሚሰቃዩ እና የህክምና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች የሕክምናው ማህበረሰብ መፍትሄ እንዲፈልግ እና የተሻለ የጤና አገልግሎት እንዲያቀርብ አስቸኳይ ጥሪ ያስፈልጋል። ለዚህም ነው የቬጂታኒ “Diabetic Foot and Wound Center” የተጀመረው።

በቬጂታኒ Diabetic Foot and Wound Center ውስጥምንአለ?

በዚህ ማእከል ውስጥ የታካሚውን ሁለንተናዊ  ጤንነት ለማስጠበቅ የተሟላ ህክምና መስጠት የሚያስችሉ አዳዲስ ዘመኑ ያፈራቸው የሕክምና መሣሪያዎች እና በሳይንስ የተረጋገጡ የህክምና ዘዴዎች እንዲሁም አሰራሮችን ያገኛሉ። እነዚህን ቴክኖሎጂዎች ከሁሉም ዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ካላቸው ዶክተሮች ጋር በማቀናጀት አገልግሎቱ ይሰጣል። ይህ አይነት አቀራረብ ባለብዙ ዲሲፒሊን በመባል የሚታዎቅ ሲሆን በተቻለ መጠን ጥሩ ውጤት ላይ ለመድረስ እውቀታቸውን እና ሙያቸውን ሳይሰስቱ የሚያጋሩ የዶክተሮች ቡድን ነው።

በቬጂታኒ የስኳር ህመምተኞች እግር እና ቁስል ህክምና ማዕከል የቴክኖሎጂ፣ ቴክኒክ እና አገልግሎቶች ውስጥ ለአብነት የሚከተሉትን ናቸው።

አገልግሎቶቻችን

  • የተበከለው ቁስል ሕክምና
  • የግፊት ቁስል ሕክምና
  • የጋንግሪን ሕክምና
  • የቆዳ ቁስል ሕክምና
  • ተላላፊ የቁስለት በሽታ ሕክምና
  • የ Venous Stasis ቁስል ሕክምና
  • እግራችን ላይ ያለ የደምቧንቧ በሽታ ሕክምና
  • በአደጋ ምክንያት ለተከሰተ ቁስል ሕክምና
  • በእሳት ወይም በፈሳሽ ነገር የተቃጠለ ቁስል
  • የቆየ ቁስል
  • የስኳር ህመም ቁስል ህክምና፣ በተለይ የስኳር በሽተኞች የእግር ቁስል ህክምና

ለቁስልሕክምናየምንጠቀምባቸውልዩልዩመሣሪያዎችእናየህክምናዘዴዎች — Special Equipment and Techniques for Diabetic Foot Ulcer Treatment

  • Hyperbaric Oxygen Therapy (HBOT) ይህ ህክምና የራሳችን growth factors በማነቃቃት ቁስሉን ከጀርም ብክለት ውጤታማ በሆነ መንገድ መከላከል እንድንችል ይረዳል። ወደ ቁስሉ የሚደርሰውን ግፊት እና ኦክስጅን በመጨመር የደም ዝውውር እንዲሻሻል፣ ሕብረ ሕዋሳትን በቶሎ እንዲያገግሙ እና የሰውነት ተግባር ወደነበረበት ለመመለስ የሚያግዝ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማሽንን የሚጠቀሙበት የሕክምና ዓይነት ነው።
  • Negative Pressure Wound Therapy (NPWT) ወይም Vacuum-Assisted Closure (VAC system) የቁስል ክትትል እና የቁስሉን ማሸጊያ የመቀየር ዘዴ ሲሆን ቁስሉ ላይ ከከባቢያዊ አየር ያነሰ የአየር ግፊት በተከፈተው ቁስል ላይ በማሳደር የቁስሉን የመዳን ሂደት የሚያፋጥን ህክምና ነው። በአሁኑ ጊዜ ሁለቱም ማለትም ከቦታ ቦታ ተንቀሳቃሽ ያልሆኑ እና ተንቀሳቃሽ የሆኑ መሣሪያዎች አሉን።
  • Wound Debridement አዲስ የህክምና ዘዴ ሲሆን የሚጠፉትን ህብረ ህዋሳት ለመቀነስ የሞተውን ሕብረ ሕዋስ ሙሉ በሙሉ ከቁስሉ ላይ በሃይድሮ ቀዶ ጥገና በማስወገድ የቁስሉን የመዳን ሂደት ያፋጥናል።
  • ኢንዶቫስኩላር ቴራፒ የስኳር ህመምተኞችን ቁስል minimally invasive የቀዶ ሕክምና ዘዴ በመጠቀም ወደ ቁስሉ የሚኖረውን የደም ፍሰትን በማሻሻል በቶሎ እንዲድን የሚያግዝ የሕክምና ዘዴ ነው።
  • የስኳር ህመምተኞች የእግር ቁስል ዳግመኛ የመከሰት እድልን ለመቀነስ ህክምናውን ላገኙ የስኳር ህመምተኞች ልዩ ጫማዎች ተሠርተዋል።

እነዚህን ሁሉ የተዘረዘሩ የአገልግሎት፣ ቴክኖሎጂዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ መሣሪያዎች አንድ ሰው በቀላሉ የሚያስፈልገኝ ይሄ ብቻ ነው ብሎ ሊያስብ ይችላል። ነገር ግን በሰዎች ሕይወት ውስጥ ሁሉንም ነገር ሊቀይሩ የሚችሉ ግን ልንለካቸው የማይንችላቸው ትናንሽ ስውር ነገሮች አሉ።

በቬጅታኒ Diabetic Foot and Wound Center የቫስኩላር ቀዶ ጥገና ሐኪም Dr. Chukij Sritongsathian እንደተናገሩት “ለተሳካ ህክምና ቁልፍ ከሆኑት ነገሮች ዋነኛው ከፍተኛ ቴክኖሎጂ ባለቤት መሆን ብቻ ሳይሆን ከቴክኖሎጂው በስተጀርባ የሚሰሩ ለስራው ፍቅሩ ያላቸው ሐኪሞች ቁርጠኝነት ነው”። ይህን ሁሉ ማወቃችሁ ቬጂታኒ ሆስፒታል ምን ያክል ጥሩ ቴክኖሎጂዎች እና ልዩ የሆኑ ቴክኒክኮችን አጣምሮ በመያዝ የተሻለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት ምን ያህል ቁርጠኝነት እንዳለው ያሳየዎታል። በተጨማሪም የቫስኩላር ቀዶ ጥገና ሐኪም፣ ኢንዶክሪኖሎጂስት፣ የአጥንት ስፔሻሊስት፣ የተላላፊ በሽታዎች ስፔሻሊስት፣ ፊዚካልቴራፒስት፣ አጠቃላይ የቀዶ ጥገና ሃኪም፣ የልብ ሐኪም፣ የኩላሊት ስፔሻሊስት እዲሁም  እንደአስፈላጊነቱ የሌሎችም ብዙ የዶክተሮች ቡድን የጋራ ዕውቀት; የቬጂታኒ የስኳር ህመምተኛች እግር እና ቁስል ማዕከልን ያካተተ በመሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል።

  • Readers Rating
  • Rated 3.5 stars
    3.5 / 5 (3 )
  • Your Rating




Related Posts