የልብ ቧንቧዎችን ለመተካት ወይም ለመጠገን የሚደረግ ቀዶ ጥገና አሁን በዓለም ዙሪያ በየቀኑ ወደመከናወን ደረጃ ደርሷል። በታይላንድ ውስጥ በቧንቧ (ቫልቭ) ምትክ ቀዶ ጥገና ሙያ ከተካኑ ሆስፒታሎች አንዱ ባንኮክ የሚገኘው ቬጅታኒ ሆስፒታል ነው።
በልብ ውስጥ የሚፈሰውን ደም የሚቆጣጠሩት የልብ ቧንቧዎች ጠርዝ በደንብ ካልተዘጋ እና ደም ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ እንዲፈስ ሲፈቅድ ወይም የልብ ቫልቭ ስቴኖሲስ ሲከሰት የቧንቧ (ቫልቭ) ምትክ ቀዶ ጥገና ያስፈልጋል።
በቬጅታኒ ሆስፒታል ውስጥ ባሉት የቀዶ ጥገና ሀኪሞች ሙያዊ እውቀት እና ችሎታ አማካኝነት ቀዶ ጥገናው በከፍተኛ የደህንነት ደረጃ ይከናወናል። ይህ ቀዶ ጥገና የታካሚዎችን ህይወት ለማራዘም እና የተሻለ የህይወት ጥራት እንዲኖራቸው ምክንያት ነው።
ሶስቱ ዋና ዋና የቧንቧ (ቫልቭ) መተካት ዘዴዎች ቲኤቪአይ (TAVI), ኤምአይኤስ (MIS) እና ክፍት የልብ ቀዶ ጥገና ናቸው። በተጨማሪም አራተኛ አማራጭ ሲኖር እሱም የቧንቧ (ቫልቭ) ጥገና ቀዶ ጥገና ይባላል። ጥገናው የበለጠ አዋጭ የሚሆንባቸው የተወሰኑ ሁኔታዎች ሲኖሩ እነዚህም የልብ ቧንቧ (ቫልቭ) በጥሩ ሁኔታ ላይ ካለ ወይም የቧንቧ (ቫልቭ) መጥበብ ችግር በሚፈጠርበት ጊዜ ነው።
በቴክኒክ እድገቶች በመታገዙ የልብ ቀዶ ጥገና ለታካሚው ደህንነቱን የተጠበቀ እና ለቀዶ ጥገና ሐኪሞችም ይበልጥ መደበኛ እየሆነ መጥቷል። እነዚህ የቀዶ ጥገና ሐኪሞች አሁን ከእነዚህ ሶስት የመተካት ሂደት አማራጮች መካከል አንዱን መምረጥ ይችላሉ ፣ ይህም ማለት አሰራሩን ከታካሚው ሁኔታ ጋር እንዲስማማ በቅርበት ማበጀት ፣ የበለጠ ምቹ ውጤትን ማረጋገጥ ፣ ታካሚውን ከማገገም በተጨማሪ የበለጠ ምቾት እንዲሰማው ማድረግ እናም ታካሚዎች ወደ መደበኛ አኗኗራቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ መመለስ እንዲችሉ ያደርጋል።
ክፍት ቀዶ ጥገና
በፊልሞች ውስጥ ብዙውን ጊዜ የሚታየው ይህ ዓይነቱ የቀዶ ጥገና ዘዴ ነው። በደረት ውስጥ አንድ ትልቅ ቀዶ ጥገና ይደረጋል፣ እና በደረት አጥንት በኩል የጎድን አጥንቶች ወደ ኋላ በመመለሻዎች ይሳባሉ፣ እና የአሰራር ሂደቱን ለማከናወን እንዲቻል ልብ ይጋለጣል።
የታካሚውን የተፈጥሮ ቧንቧ (ቫልቭ) ለመተካት ዲስኮችን የሚመስሉ ሰው ሰራሽ ቧንቧዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ። እነዚህ ቧንቧዎች ወደ ልብ ውስጥ በሚገባ ደምን እያጣራ የሚያሰራጭ የልብ ክፍል (ቬንትሪክል) መጨረሻ ላይ ይጣበቃሉ። በእነሱ ውስጥ የሚፈሰው የደም መፍሰስ ተግባር የአዲሶቹን ቧንቧዎች መከፈትና መዘጋት ይቆጣጠራል።
ክፍት ቀዶ ጥገና እንደተለምዶው ከቀዶ ጥገናው በኋላ በሆስፒታል ውስጥ የአንድ ሳምንት ቆይታ እና በአጠቃላይ ከስምንት እስከ አስራ ሁለት ሳምንታት አካባቢ የማገገሚያ ጊዜ ያስፈልገዋል።
ትራንስካቴተር አኦርቲክ ቫልቭ ኢምፕላንቴሽን (ቲኤቪአይ)
ቲኤቪአይ (TAVI) ቀጭን ካቴተር ወይም ቱቦ በሰውነት ውስጥ ባለው የደም ቧንቧ ውስጥ በተለይም በላይኛው እግር ወይም በደረት ውስጥ ማስገባትን ያካትታል። ካቴቴሩ ወደ ወሳጅ ቧንቧ እንዲገባ ይደረጋል፣ እዚያም ተፈጥሯዊውን
የሚተካ ሰው ሰራሽ ቧንቧ (ቫልቭ) ለመምራት እና ለመጠገን ያገለግላል።
ቲኤቪአይን መምረጥ ጥቅሞች አሉት፣ ልብን ማስቆም ስለማያስፈልግ ታካሚውን በልብ-ሳንባ ማለፊያ መሳሪያ ላይ ማድረግ አያሻም። እናም አሰራሩ በደረት ላይ ትልቅ መቀደድን ፣ ከዛም ጋር ተያይዞ የሚመጣ የህዋስ ጉዳት እና ረጅም የሆነ የማገገምያ ምዕራፍ አያኖረውም።
ክፍት የልብ ቀዶ ጥገናን ለማድረግ አስጊ ሲሆን ነገር ግን ቧንቧ (ቫልቭ) መተካት የግድ የሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች በሚኖሩ ጊዜ ቲኤቪአይ (TAVI) የቀዶ ጥገና ሐኪሙ ምርጫ ነው።
ሚኒማሊ ኢንቬሲቭ ቀዶ ጥገና (ኤምአይኤስ)
ኤምአይኤስ ቀዶ ጥገና የሚካሄደው እንደ ክፍት የልብ ቀዶ ጥገና ሳይሆን ፣ በደረት በቀኝ በኩል ወደ ልብ ለመድረስ በጎድን አጥንት በኩል ብዙ ትናንሽ ቀዳዳዎችን በማድረግ ነው። ኤምአይኤስን በቀዶ ሕክምና ሐኪሞችም ሆነ በታካሚዎቻቸው ዘንድ ተወዳጅ እንዲሆን የሚያደርጉት ብዙ ጥቅሞች አሉት።
ቁስሎቹ ያነሱ ስለሆኑ በኤምአይኤስ ቀዶ ጥገና ወቅት የሚኖረው የደም መፍሰስ ከክፍት ቀዶ ጥገና አንፃር ያነሰ ስለሆነ አነስተኛ የደም ምትክ ያስፈልገዋል። ትንሽ ቀዳዳ መሆኑ ደግሞ የመበከል እድሉን ስለሚቀንስ በአካባቢው ሕብረ ሕዋሳት ላይ የሚደርሰው ጉዳት ያነሰ ይሆናል በተጨማሪም ታካሚው ሲያገግም ሊኖር የሚችለውን ህመም ይቀንሳል። ይህም በሆስፒታሉ ውስጥ አጭር ቆይታን ፣ በአጠቃላይ ፈጣን ማገገምን ፣ የታካሚውን መደበኛ እንቅስቃሴዎች እና የአኗኗር ዘይቤዎች በፍጥነት መመለስን ያመለክታል። እንዲሁም በደረት ላይ የሚኖሩ ጠባሳዎች እምብዛም የማይታዩ ይሆናሉ ማለት ነው።
የቧንቧ (ቫልቭ) ጥገና አማራጭ
ምንጊዜም በተቻለ መጠን የታካሚውን ነባር የልብ ሕብረ ሕዋስ መጠገን ተቀዳሚ ምርጫ ነው።
ለልብ ቧንቧ (ቫልቭ) ቀዶ ጥገና ቬጅታኒ ሆስፒታልን ያነጋግሩ
ለልብ ቧንቧ (ቫልቭ) ምትክ እና ጥገናን ለማድረግ ሶስት ዘዴዎች ሲኖሩ ባንኮክ የሚገኘው ቬጅታኒ ሆስፒታል የልብ ቧንቧ (ቫልቭ) ቀዶ ጥገና ከሚያከናውኑ ከፍተኛ የህክምና ተቋማት አንዱ ነው። ከዶክተር ጋር የምክክር ክፍለ ጊዜ ለማስያዝ ቬጅታኒ ሆስፒታልን ያነጋግሩ።
- Readers Rating
- Rated 5 stars
5 / 5 (Reviewers) - Spectacular
- Your Rating