የአጥንት መቅኒ ንቅለ ተከላ ወይም ትራንስፕላንት (ስቴም ሴል) እንዴት ካንሰርን ለማከም ጥቅም ላይ ይውላል - Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand.

የጤና መረጃዎች

የአጥንት መቅኒ ንቅለ ተከላ ወይም ትራንስፕላንት (ስቴም ሴል) እንዴት ካንሰርን ለማከም ጥቅም ላይ ይውላል

Share:

የአጥንት መቅኒ ንቅለ ተከላ ወይም ቢኤምቲ (BMT) ፣ እንዲሁም ሄማቶፖይቲክ ስቴም ሴል ትራንስፕላንት ወይም ኤች.ኤስ.ሲ.ቲ (HSCT) በመባል የሚታወቀው፣ የተጎዳ ወይም የታመመ መቅኒ በጤናማ ግንድ ሕዋስ (ስቴም ሴል) መተካትን የሚያካትት የህክምና ሂደት ነው። ይህ ሕክምና የተለያየ የደም ሕመም፣ ካንሰር እና የበሽታ መከላከል ችግር ላለባቸው ታካሚዎች ሕይወት አድን ሊሆን ይችላል። እዚህ በቢኤምቲ ሊታከሙ ስለሚችሉ አንዳንድ ሁኔታዎች ዝርዝር መግለጫ እናቀርባለን።

የአጥንት መቅኒ ንቅለ ተከላ ወይም ትራንስፕላንት ለህክምና የሚውለው፡-

  • የአጥንት መቅኒ ወይም ግንድ ሕዋስ (ስቴም ሴል) ተጎድተው ጤናማ የደም ሴሎችን ማምረት ካልቻሉ
  • የአጥንት መቅኒ ወይም የደም ሕዋሶች ጤናማ ካልሆኑ ወይም ሕመምተኞች ጤናማ የግንድ ሕዋስ (ስቴም ሴል) ለመተካት የሚያስገድድ ሕመም ሲኖራቸው
  • ከፍተኛ መጠን ያለው ኬሞቴራፒ ወይም ጨረራ ከተወሰደ በኋላ እና ሁለቱንም የካንሰር ሕዋሳት እና ጤናማ ሕዋሶች ላይ ተፅዕኖ ይኖራል። ይህ ደግሞ የግንድ ሕዋስ (ስቴም ሴል) ንቅለ ተከላ ወይም ትራንስፕላንት ያስፈልገዋል።

የግንድ ሕዋሶች ወይም ስቴም ሴሎች በአጥንት መቅኒ ውስጥ እና በአጥንት ለስላሳ ሕብረ ሕዋሳት እንዲሁም በእምብርት ገመድ ውስጥ ያድጋሉ። ለተወሰነ ጊዜ ካደጉ በኋላም ወደሚከተሉት ይለወጣሉ:-

  • ፕሌትሌትስ የደም መርጋትን ለመከላከል
  • ቀይ የደም ሴሎች በደም ውስጥ ለንጹህ ኦክስጅን
  • ነጭ የደም ሴሎች የውጭ በሽታዎችን ለመዋጋት የበሽታ መከላከያ እድገት

የግንድ ሕዋስ (ስቴም ሴል) ሕክምና እንዴት ይሠራል?

ሁለት ዓይነት ንቅለ ተከላዎች ሲኖሩ ለታካሚው የትኛው የተሻለ እንደሆነ ሐኪሙ ይወስናል።

  • አውቶሎገስ (AUTO) ንቅለ ተከላ ወይም ትራንስፕላንት

ይህ ከአጥንት መቅኒ ወይም ከደም የተገኘ ጤናማ የግንድ ሕዋሶች ወይም የስቴም ሴሎች ስብስብ ነው። ከዚያም ዶክተሮች በማቀዝቀዝ በጥንቃቄ ያስቀምጧቸዋል። ከፍተኛ መጠን ያለው የኬሞቴራፒ ሕክምና ከተደረገ በኋላ ሕዋሶቹ በደም ስር (አይቪ) በኩል ደም ውስጥ በመግባት ወደ መቅኒ ይመለሳሉ። ይህም የአጥንት ቅልጥሞች ጤናማ የደም ሕዋሶችን እንደገና እንዲያመርቱ እና በሰውነት ውስጥ ያለውን በሽታ የመከላከል አቅምን በቡድን እንዲያሰባስቡ ያስችላቸዋል።

  • አሎጄኒክ ወይም አሎ (ALLO) ንቅለ ተከላ ወይም ትራንስፕላንት

ይህ የሚደረገው ከለጋሾች ጤናማ የአጥንት መቅኒ በመውሰድ ነው። ደም ከመውሰዱ በፊት የለጋሽ አጥንት መቅኒ ከታካሚው መቅኒ ጋር የሚጣጣም መሆኑ በጣም አስፈላጊ ነው። ይህ ካልሆነ የታካሚው አካል የተተከሉትን ሕዋሶች ካላወቀ ውድቅ ይሆናል። የቤተሰብ አባል ለጋሽ ለመሆን ከሁሉ የተሻለ ምርጫ መሆን አለበት። አሎ ከመውሰዱ በፊት ኬሞቴራፒ ፣ ራዲዮቴራፒ ወይም የሁለቱ ሕክምናዎች ጥምረት የድሮውን ግንድ ሕዋሶች ወይም ስቴም ሴሎች በአዲስ ለመተካት አስቀድሞ መሰጠት አለበት።

የእምብርት ገመድ ደም ንቅለ ተከላ (ትራንስፕላንት) ከአሎጄኒክ ንቅለ ተከላ (ትራንስፕላንት) ጋር ይመስላል። ነገር ግን ልዩ የሚያደርገው ነገር የሚለገሰው ከህፃን እምብርት መሆኑ ነው። ስለዚህ ከግንድ ሕዋስ (ስቴም ሴል) ጋር ከመመዋሃዱ በፊት የኬሞቴራፒ ሕክምናን የመቀበል እድሉ አነስተኛ ነው። ታካሚው ተገቢውን ለጋሽ ማግኘት በማይችልበት ጊዜ ዶክተሩ ይህንን የግንድ ሕዋስ (ስቴም ሴል) ለህክምና መጠቀም ይኖርበታል። ነገር ግን የተለገሱ ሕዋሶች ከታካሚው አካል ውጭ ስለሚወሰዱ ለችግር የመጋለጥ ስጋት ምንጊዜም ይኖራል።

ስጋቶቹ ምንድን ናቸው?

ከአውቶሎገስ ወይም ከአሎጄኒክ ንቅለ ተከላ በፊት ታካሚው አስቀድሞ ከፍተኛ መጠን ያለው የኬሞቴራፒ ሕክምና ያስፈልገዋል። ስለዚህ እሱ ወይም እሷ በሚከተሉት የኬሞቴራፒ የጎንዮሽ ጉዳቶች ሊሰቃዩ ይችላሉ:-

  • ማቅለሽለሽ
  • ከባድ ኢንፌክሽኖች
  • ማስታወክ
  • ድካም
  • የደም መፍሰስ

በእነዚህ የጎንዮሽ ጉዳቶች መሰቃየት ለታካሚው ጥሩ ባይሆንም ነገር ግን ይህ የግንድ ሕዋስ (ስቴም ሴል) ንቅለ ተከላ (ትራንስፕላንት) ከተደረገ በኋላ ኃይለኛ ምልክቶችን ይከላከላል።

በአሎ (ALLO) ንቅለ ተከላ (ትራንስፕላንት) ውስጥ ታካሚው የግንድ ሕዋሶች (ስቴም ሴሎች) ከለጋሽ ወይም ከእምብርት ደም ከተቀበለ በኋላ በሰውነት ውስጥ ያሉት ሕዋሶች ከውጭ ሕዋሶች ጋር ስለሚዋጉ በጂ.ቪ.ኤች.ዲ (GVHD) የመያዝ አደጋ አለ። ምንም እንኳን ዶክተሮች ለጋሽ ግንድ ሕዋስ (ስቴም ሴል) ከመውሰዱ በፊት ከታካሚው ጋር መመሳሰልን ቢያረጋግጡም ይህ ከንቅለ ተከላ (ትራንስፕላንት) በኋላ ወዲያውኑ ወይም ከአንድ አመት በኋላ ሊከሰት ይችላል።

ታካሚው በዚህ ችግር የሚሰቃይ ከሆነ የረጅም ጊዜ መድሃኒቶች ምልክቶቹን ለመቆጣጠር ይረዳሉ።
ግንድ ሕዋሶች (ስቴም ሴሎች) ከሌሉ ሰውነት ደምን እና የሰውነትን በሽታ የመከላከል ስርዓትን ለመስራት የሚያስፈልጉትን ንጥረ ነገሮች ማምረት አይችልም። በግንድ ሕዋስ (ስቴም ሴል) ንቅለ ተከላ (ትራንስፕላንት) ጊዜ ሰውነት ከጤናማ የስቴም ሴሎች ጋር በመዋሃድ “ይድናል”።

ትክክለኛውን የግንድ ሕዋሶች (ስቴም ሴሎች) መምረጥ ውስብስብ ቢሆንም ሐኪሙ የትኛውን ስቴም ሴሎች የመሰብሰብ ዘዴ ለህክምና ጥቅም ላይ መዋል እንዳለበት ይወስናል።

  • Readers Rating
  • Rated 5 stars
    5 / 5 (1 )
  • Your Rating