የኮሎሬክታል ወይም አንጀት ካንሰር፡- ቀደም ብሎ መለየት ወደ ፈጣን ህክምና ይመራል - Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand.

የጤና መረጃዎች

የኮሎሬክታል ወይም አንጀት ካንሰር፡- ቀደም ብሎ መለየት ወደ ፈጣን ህክምና ይመራል

Share:

የኮሎሬክታል ወይም አንጀት ካንሰር ከሁሉም የካንሰር አይነቶች 4ኛው በብዛት ከሚገኝ ካንሰር ነው። ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሞት መጠኑ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል ምክንያቱም “ኮሎኖስኮፒ” በተባለ የማጣሪያ ምርመራ በመገኘቱ ምክንያት ነው።

የኮሎሬክታል ካንሰር የሚከሰተው በአንጀት (ኮሎን) ውስጥ ትንንሽ ዕጢ ወይም ፖሊፕ በመኖሩ ምክንያት ነው። በመነሻ ደረጃ ላይ ምንም ምልክቶች አይታዩም ፤ ነገር ግን ፖሊፖች ሲያድጉ እና ወደ ካንሰር ሲቀየሩ ምልክቶች መታየት ይጀምራሉ። ምልክቶቹ በሰገራ ውስጥ ደም የተቀላቀለ ንፍጥ፣ የሰገራ ማነስ፣ ተለዋዋጭ የሆድ ድርቀት እና ተቅማጥ፣ የሆድ ድርቀት መጨመር፣ የሆድ መነፋት ወይም በሆድ ውስጥ የሚታይ እብጠት ይገኙበታል።

ስለሆነም ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች በየጊዜው የኮሎንኮፒ ምርመራ ካደረጉ በሽታው ቀደም ብሎ ስለሚታወቅ ታማሚዎቹ አፋጣኝ ሕክምና እንዲያገኙ ያስችላል።

ለኮሎሬክታል ካንሰር የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ የሆኑ ሰዎች ኮሎንኮስኮፒን በሚከተለው መልኩ እንዲወስዱ ይመከራሉ:-

  • ከ 50 ዓመት በላይ የሆናቸው ሰዎች በየ 3-5 ዓመቱ ኮሎንኮስኮፒ እንዲያደርጉ ይመከራሉ
  • የአንጀት እንቅስቃሴ ላይ ችግር ያለባቸው ፤ እንደ ሆድ ድርቀት ወይም ተደጋጋሚ ተቅማጥ ወይም ተለዋዋጭ የሆድ ድርቀት እና ተቅማጥ
  • ደም ያለበት ሰገራ ፣ ደማቅ ቀይ ወይም ጥቁር ቀለም ያለው እና ያልተለመደ ሽታ ሊኖረው ይችላል
  • ፊንጢጣ አካባቢ ያሉ ዕጢዎች ወይም ፖሊፕች ሰገራ በማማጥ ጊዜ ሊቀደዱ ይችላሉ ፤ ይህም የደም መፍሰስ ሊኖረው ይችላል
  • የሆድ መወጠር ፣ መነፋት እና ህመም
  • የሆድ እብጠት ፣ የክብደት መቀነስ ፣ የቆዳ መገርጣት እና ድካም

ለበለጠ መረጃ፡-እባኮትን የላይፍ ካንሰር ማዕከልን በቬጅታኒ ሆስፒታል ያነጋግሩ;- ስልክ. 02-734-0000
የአማርኛ ስልክ መስመር: (+66) 90-907-2560

  • Readers Rating
  • Rated 3.7 stars
    3.7 / 5 (3 )
  • Your Rating