የአከርካሪ አጥንት ስቴኖሲስ (Spinal Stenosis) ወይም የአከርካሪ አጥንት ቦይ መጥበብ በአረጋውያን ላይ በብዛት የሚገኝ በሽታ ነው። በሽታው በአከርካሪ አጥንት አካባቢ ውስጥ የሚገኙትን ዲስኮች ፣ ጅማቶች እና መገጣጠሚያዎችን የሚጎዳው በአከርካሪ አጥንት መበላሸት ምክንያት ነው።
የአከርካሪ አጥንት ቦይ ከእድሜ ጋር እየጠበበ ይሄዳል ፤ ምናልባትም ነርቮችን እስከሚጨምቅበት ደረጃ ይደርሳል። የነርቭ መጨናነቅ ከሚከተሉት ምልክቶች አንዱን ሊያስከትል ይችላል:-
- የዳሌ እና የወገብ ህመም
- ከረጅም የእግር ጉዞ በኋላ የሚባባስ የእግር ህመም
- ወደ ኋላ በሚታጠፍ ጊዜ የሚባባስ እና በእረፍት ጊዜ ወይም ወገብን ወደ ፊት በማጠፍ የሚቀንስ የጀርባ ህመም (Back pain)
የጀርባ ህመም (Back pain) ላጋጠማቸው እና ባልታወቀ ምክንያት የመራመድ ችግር ላጋጠማቸው አረጋውያን ታካሚዎች ተገቢውን ህክምና እንዲያገኙ ለእያንዳንዱ ታካሚ ልዩ ባለሙያተኛን በማማከር ለምርመራ እንደ ኤክስሬይ እና ኤምአርአይ ያሉ ምርመራዎችን ማድረግ አስፈላጊ ነው።
ለበለጠ መረጃ እባክዎን የአከርካሪ አጥንት ማዕከልን፣ በቬጅታኒ ሆስፒታል ያነጋግሩ።
ይደውሉ፡ 02-734-0000 Ext. 5500
የአማርኛ ስልክ መስመር: (+66) 0- 90-907-2560
ኢሜል፡ [email protected]
- Readers Rating
- Rated 5 stars
5 / 5 (Reviewers) - Spectacular
- Your Rating