የሽባነት (paralysis) ወይም መንቀሳቀስ አለመቻል (paresis) ስጋትን ለመቀነስ አይስኬሚክ ስትሮክን (Stroke)ወዲያውኑ ያክሙ - Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand.

የጤና መረጃዎች

የሽባነት (paralysis) ወይም መንቀሳቀስ አለመቻል (paresis) ስጋትን ለመቀነስ አይስኬሚክ ስትሮክን (Stroke)ወዲያውኑ ያክሙ

Share:

ሴሬብሮቫስኩላር በሽታ (Cerebrovascular Disease) ወይም ስትሮክ (Stroke) ለሽባነት (paralysis) ወይም መንቀሳቀስ አለመቻል (paresis) ዋና መንስኤዎች ናቸው። በሽታው ያለባቸው ሰዎች በድንገተኛ ጥቃቶች የሚሰቃዩ ሲሆን የሕክምና ክትትል በወቅቱ ማግኘት የፈውስ እድልን ይጨምራል።

በቬጅታኒ ሆስፒታል የነርቭ ቀዶ ሐኪም የሆኑት ዶክተር ፖንግሳኮርን ፖንግሳፓስ እንዳስረዱት ሴሬብሮቫስኩላር በሽታ (Cerebrovascular Disease) ወይም ስትሮክ (Stroke) የሚከሰተው በደም ወሳጅ ቧንቧዎች መዘጋት ወይም በአንጎል ውስጥ ያሉ የደም ስሮች መጥበብ ወይም መቀደድ ሳቢያ ወደ አንጎል የደም ዝውውር እንዲስተጓጎል በማድረግ የተወሰኑ ምልክቶች እንዲታዩ ያደርጋል ፤ ይህም እንደ የፊት ሽባ መሆን፣ ብዥ ያለ እይታ፣ ድርብ እይታ፣ ድክመት፣ መደንዘዝ ወይም በአንድ የአካል ክፍል ላይ የሚከሰት ሽባነት (paralysis) ፣ የደበዘዘ ንግግር ወይም መናገር አለመቻልን ያካትታል። የስትሮክ (Stroke) በሽታ የሚከሰተው በመካከለኛ እና በእድሜ የገፉ ሰዎች ላይ ነው ፤ ነገር ግን የደም ስሮቻቸው በእድሜ መበላሸታቸው ምክንያት ሁኔታው ​​በአረጋውያን ላይ በብዛት ይታያል።

የስትሮክ (Stroke) ስጋት ምክንያቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:

  1. የደም ግፊት፡- ረዘም ላለ ጊዜ ከ140/90 ሚሜ ኤችጂ በላይ የደም ግፊት ያላቸው ሰዎች የደም ስሮቻቸው ከአማካይ በበለጠ ፍጥነት ይበላሻሉ። ይህ የደም ቧንቧ መዘጋት ፣ መጥበብ (ስቴኖሲስ) ወይም የደም ስሮች መቀደድ አደጋን ከፍ ያደርገዋል።
  2. የስኳር በሽታ፡- የደም ቧንቧ መበላሸት ያስከትላል፣ ይህም ከስትሮክ (Stroke) ጋር የተገናኙ ችግሮችን ይጨምራል።
  3. የልብ ሕመም፡- መደበኛ ያልሆነ የልብ ምት (ሀርት አሪዝሚያ) ፣ የሴፕታል እክል እና አይስኬሚክ ካርዲዮሚዮፓቲ ያካትታል ፤ እነዚህም በአንጎል ውስጥ የደም መርጋትን የሚያስከትሉ ሲሆን ይህም የሚፈጠረው ወደ ደም ስሮች እና ደም ወሳጅ ቧንቧዎች በመዛመት እና በመዘጋት ነው
  4. ሃይፐርሊፒዲሚያ፡- የሚያቃጥል ምላሽን በማምጣት እና በደም ወሳጅ ቧንቧ ግድግዳዎች ላይ የስብ ክምችቶችን በመፍጠር ደም ስሮች እንዲበላሹ በማድረግ የመዘጋት ፣ መጥበብ (ስቴኖሲስ) ወይም መቀደድ አደጋን ያስከትላል።
  5. ማጨስ፡- ሲጋራ በአንጎል ውስጥ የደም ስሮች መበላሸትን የሚያፋጥኑ ኬሚካሎች አሉት። “ብዙ ባጨሱ ቁጥር ስትሮክ (Stroke) ይጨምራል” እንደሚባለው አጫሾች ከማያጨሱ ሰዎች ይልቅ ለስትሮክ የመጋለጥ እድላቸው በስድስት እጥፍ ከፍ ያለ ነው።
  6. አልኮልን በብዛት መጠጣት፡- የልብ አሰራር ብልሽትን ያስከትላል ፤ ይህም ወደ አዕምሮ ደም ስሮች እንዲሰራጭ ልማሞ እና የደም መርጋት በማስከተል እንዲዘጋ ያደርጋል።
  7. ከመጠን በላይ መወፈር እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማነስ፡- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የደም ስሮችን፣ የደም ቧንቧዎችን እና የልብን ውጤታማነት ይጨምራል። ስትሮክን (Stroke) ለመከላከል እና የልብ ስራን በተሻለ ሁኔታ እንዲሰራ ያደርጋል ፤ ይህም ለስትሮክ (Stroke) የመጋለጥ እድልን በእጅጉ ይቀንሳል።

ስትሮክ (Stroke) በሲቲ ስካን፣ ኤምአርአይ እና ኤምአርኤ፣ ትራንስክራኒያል ዶፕለር ወይም ቲሲዲ (TCD) እና ካሮቲድ ዶፕለር ከሌሎች ተጨማሪ ዘዴዎች ጋር ሊታወቅ ይችላል። ትክክለኛ ምርመራ ዶክተሮች ውጤታማ የሆነ የመከላከያ እና የሕክምና እቅድ እንዲያወጡ ይረዳል።

ስትሮክን (Stroke) ለማከም ያለው መርህ የአንጎል ሴሎችን ረጅም ዕድሜ እና ህልውና መጠበቅ ነው። በደም ስሮች ውስጥ በቂ እና ያልተቋረጠ የደም ዝውውር የአንጎል ህዋሶች በፍጥነት እንዲያገግሙ ያስችላቸዋል ፤ ይህም ታካሚዎች ወደ መደበኛ የጤና ሁኔታቸው እንዲመለሱ ያደርጋል። ዶክተሩ በስትሮክ (Stroke) ሕክምና የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ክሊኒካዊ ግምገማ ይጀምራል።  ፀረ-ደም መርጋት መድኃኒቶችን ያለ ገደብ እንደ ሕክምና ለመውሰድ ጠቋሚዎች ካሉ ፤ ምልክቶቹ ከተከሰቱ በኋላ በ 4.5 ሰዓታት ውስጥ ዶክተሩ ወደ አንጎል የደም አቅርቦትን የሚዘጋውን የደም መርጋት ለማስቆም መድኃኒቶቹን ያዝዛል። ነገር ግን በትልልቅ የደም ስሮች ውስጥ መዘጋት ካለ ሐኪሙ በሜካኒካል ትሮምቤክቶሚ ያክማል። አሰራሩ የደም መርጋትን ለማስወገድ ብሽሽት ላይ ትንሽ ቀዳዳ በመፍጠር በዛ ውስጥ አልፎ ወደ አንጎል በሚያመሩት ደም ስሮች ውስጥ ካቴተር ማስገባትን ያካትታል። ሜካኒካል ትሮምቤክቶሚ በፍጥነት የሚከናወን የኢንዶቫስኩላር ቴክኒክ ሲሆን ይህም የአንጎል ስራን በመጠበቅ አነስተኛ ጉዳት ያስከትላል።

ታካሚዎች በስትሮክ (Stroke) በሽታ የመያዝ እድልን ለመቀነስ በሚከተሉት መንገዶች  ከአደጋ መንስኤዎች መራቅ አለባቸው፡-

  • የደም ግፊትን በመደበኛ ክልል ውስጥ ማቆየት
  • በኮሌስትሮል እና ቅባቶች የበለፀጉ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ
  • ማጨስን እና የአልኮል መጠጦችን ማስወገድ
  • የስኳር ህመምተኞች የስኳር መጠን መቆጣጠር
  • የሰውነት ክብደትን ጤናማ በሆነ ክልል ውስጥ ማቆየት
  • ተጨማሪ አትክልትና ፍራፍሬ መመገብ
  • አዘውትሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

“ስትሮክ (Stroke) በታካሚዎች የህይወት ጥራት እና በአካባቢያቸው ሰዎች ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል። ስለዚህ የራሳቸውን ጤና ከመጠበቅ በተጨማሪ ሌላው አስፈላጊ ነገር ያልተለመዱ ምልክቶችን መከታተል ነው። ምክንያቱም በሽታው ቀደም ብሎ ከታወቀ ማከም ይቻላል ፤ ይህም ሽባነትን (paralysis) ሊቀንስ ይችላል። “ ዶክተር ፖንግሳኮርን

  • Readers Rating
  • Rated 4.8 stars
    4.8 / 5 (2 )
  • Your Rating