የቀዶ ጥገና ሕክምና ማዕከል
የሬዙም የውሃ ትነት ሕክምና – ምንም ቀዶ ጥገና ሳያስፈልግ ለቤኒን ፕሮስታቲክ ሃይፐርፕላዝያ ወይም ፕሮስቴት እጢ የሚደረግ ዘመናዊ ሕክምና
ቤኒን ፕሮስታቲክ ሃይፐርፕላዝያ ወይም የፕሮስቴት እጢ የሽንት ችግር ምልክቶችን ለምሳሌ እንደ ዳይሱሪያ ፣ ብዙ ጊዜ በሌሊት ሽንት ፣ እንዲሁም ፊኛን ባዶ አለማድረግ ወይም ሽንትን መያዝ አለመቻልን ያስከትላል። እነዚህም የታካሚዎችን የዕለት ተዕለት ሕይወት ሊያስተጓጕሉ ይችላሉ።