ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መሰረት ብዙ አይነት ህክምናዎችን እናቀርባለን።
- ለጆሮ ፣ አፍንጫ እና ጉሮሮ በሽታዎች እንደ ሳይነስ (Sinusitis፣ የቶንሲል ሕመም (Tonsillitis) እና አለርጂክ ሪህናይትስ (Allergic Rhinitis) የመሳሰሉ ምርመራዎች እና አጠቃላይ ህክምና
- ኦቶላሪንጎሎጂ (Otolaryngology): የጆሮ ፣ አፍንጫ እና ጉሮሮ (ENT) መታወክ እንዲሁም ከራስ እና አንገት ጋር ለሚገናኙ በሽታዎች የቀዶ ጥገና ሕክምና እና አጠቃላይ
- የታይሮይድ ዕጢ ቀዶ ጥገና ሕክምና
- የአፍ ውስጥ ካንሰር ሕክምና
- የመዋጥ መታወክ፣ የድምጽ መታወክ፣ መጥፎ የአፍ ጠረን እና የፊት መደንዘዝ ሕክምና
- የመስማት ችሎታ ምርመራ እና የሚዛን መዛባት ምርመራ
- እንደ የንግግር መታወክ እና መንተባተብ ያሉ የንግግር እክሎችን መመርመር
- የመስማት እና የንግግር እክል ምርመራ እና ሕክምና
- የአጉሊ መነጽር / ኤንዶስኮፒክ ምርመራ
- ከፍተኛ እና መለስተኛ የጆሮ፣ አፍንጫ እና ጉሮሮ ቀዶ ጥገናዎች
- የሕፃናት የጆሮ፣ አፍንጫ እና ጉሮሮ ምርመራ
- መካከለኛው የጆሮ ክፍል ቀዶ ጥገና
- ኤንዶስኮፒክ የሳይነስ ቀዶ ጥገና
- ውስጣዊ ጆሮ እና የነርቭ ሥርዓት ምርመራ
- ሬድዮ ፍሪኩዌንሲ ተርቢኖፕላስቲ