የሕፃናት የነርቭ ሳይንስ እና ማገገሚያ ማዕከል - Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand.

የሕፃናት የነርቭ ሳይንስ እና ማገገሚያ ማዕከል

ሁሉን አቀፍ የሆነው የሕፃናት ነርቭ ሳይንስ እና ማገገሚያ ማዕከል ንደ ሴሬብራል ፓልሲ (Cerebral Palsy) ፣ የሚጥል በሽታ (Epilepsy)፣ ኦቲዝም (Autism) ፣ ዳውን ሲንድሮም (Down Syndrome) ፣ የመማር እና የባህርይ ውስንነት እንዲሁም አቴንሽን ዴፊሲት ሃይፐር አክቲቪቲ ዲስኦርደር ወይም ኤ.ዲ.ኤች.ዲ (ADHD) እና የእድገት መዘግየት የመሳሰሉ የነርቭ እና የመንቀሳቀስ ችግር ላለባቸው ህጻናት የተቀናጀ እና የላቀ የህክምና አገልግሎት ይሰጣል።
ማዕከሉ በወላጆች እና በህክምና ቡድኑ መካከል ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ተመሳሳይ ግቦችን ለማሳካት ከፍተኛ የህክምና መሳሪያዎችን እና የአካል ቴራፒስቶች ፣የሙያ ቴራፒስቶች ፣ የንግግር ቴራፒስቶች እና የእድገት አበረታቾችን ጨምሮ ልምድ ያላቸው ልዩ ባለሙያተኞች እና ሁለገብ ባለሙያዎች ቡድን አሉት ።

የአገልግሎት ሰዓታት

ሰኞ - እሁድ : 08.00 am - 07.00 pm

ቦታ

የሕፃናት የነርቭ ሳይንስ እና ማገገሚያ ማዕከል፣ 12ኛ ፎቅ ህንፃ 1 ፣ ቬጅታኒ ሆስፒታል

ቀጠሮዎች እና ጥያቄዎች

ይደውሉ: (+66)2-734-0000 Ext. 2316, 2332
የአማርኛ ስልክ መስመር: (+66)90-907-2560

ማዕከሉ የተለያዩ የስሜት ህዋሳትን በማነቃቃት ህጻናት እንዲያገግሙ የሚያግዝ በባለብዙ-ስሜታዊ አካባቢ ወይም ስኖዝለን (Snoezelen rooms) ክፍሎች አሉት። በተጨማሪም መጫወቻ ሜዳ፣ ቨርቹዋል ኢንተራክቲቭ ወይም መስተጋብራዊ ክፍል (Virtual Interactive room) እና የነርቭ ህመም ያለባቸውን ልጆች ለማከም እና እድገታቸውን በተለያዩ ዘርፎች ማለትም እንደ እጅ ተግባር፣ መቆም እና መራመድ፣ ተግባቦት ፣ ባህሪ ማሻሻያ እና መማርን እንዲያዳብሩ በሮቦት የታገዘ ስልጠና አለው።

ስኖዝለን ክፍል (ሁሉንም 5 የስሜት ህዋሳት ለማነቃቃት የተነደፈ ባለብዙ ክፍል ቴራፒ)
ሴሬብራል ፓልሲ የሚከሰተው በጨቅላነት ወይም በልጅነት ጊዜ አዕምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ሲጎዳ ነው። ይህ የእድገት መዘግየቶችን ያስከትላል፤ በተለይም በእንቅስቃሴ፣ በመግባባት፣ በመማር ፣ በባህሪ እና በዕለት ተዕለት ሕይወት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። በአሁኑ ጊዜ ስኖዝለን ክፍልን (Snoezelen room) የሚያካትት የመድሐኒት እና የአካል ሕክምና መርሃ ግብርን ጨምሮ የተለያዩ የሕክምና አማራጮች አሉ። ይህም ሴሬብራል ፓልሲ ያለባቸው ህጻናት የአምስቱንም የስሜት ህዋሳት ለማነቃቃት የተነደፈ ሁለገብ ቴራፒ ክፍል ማየት፣ መስማት፣ መዳሰስ፣ ማሽተት እና የጣዕም ክህሎቶቻቸው እንዲዳብሩ ለመርዳት ነው።

ስሜታዊ እድገትን፣ እንቅስቃሴን እና እራስን የመርዳት ችሎታን ለማዳበር የሚረዱ ክፍሎች

  • ኦቲዝም ያለባቸው ልጆች
  • ሴሬብራል ፓልሲ ያለባቸው ልጆች
  • ዳውን ሲንድሮም ያለባቸው ልጆች
  • ጥሩ የሞተር ችሎታዎች፣ አጠቃላይ የሞተር ችሎታዎች፣ የመራመድ እና የአቀማመጥ እድገት መዘግየት ያለባቸው ልጆች
  • የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን የሚነኩ የመማር ችግር፣ የባህሪ ችግር እና የአዕምሮ እክል ያለባቸው ልጆች

ስኖዝለን ክፍል (Snoezelen room) ብርሃን፣ ቀለም፣ ድምጽ፣ መዓዛ እና ንክኪን ጨምሮ የተለያዩ የስሜት ህዋሳትን በብዙ ስሜት ቀስቃሽነት የሚያነቃቃ አስመሳይ አካባቢ ሲሆን በበርካታ አካባቢዎች ውስጥ የእድገት ማነቃቂያዎችን የበለጠ ውጤታማ ያደርጋል፤ ይህ የሕክምናውን ቆይታ በመቀነስ ወደ ተሻሻሉ የሕክምና ውጤቶች ያመራል። የስኖዝለን ክፍል (Snoezelen room) የሚከተሉትን ጨምሮ በተለያዩ ገጽታዎች እድገትን ሊያበረታታ ይችላል-

እንቅስቃሴ

ሴሬብራል ፓልሲ ያለባቸው ህጻናት በጡንቻ ድክመት፣ ጥንካሬ እና የእንቅስቃሴ ቅንጅት እጦት ምክንያት ያልተለመዱ የእንቅስቃሴ ዘይቤዎች ይኖራቸዋል። የስኖዝለን ክፍል (Snoezelen room) የእንቅስቃሴ ማነቃቂያ መሳሪያዎችን እንደ የመዳሰሻ ሰሌዳዎች ፣ የውሃ አልጋዎችን ሚዛን ለመቆጣጠር እና በብርሃን የሚመራ የእንቅስቃሴ እንቅስቃሴዎችን በመጠቀም እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ይረዳል ።

መግባባት

ሴሬብራል ፓልሲ ያለባቸው ልጆች እንደ ግልጽ ያልሆነ ንግግር ያሉ የመግባቢያ ችግሮች ያጋጥማቸዋል። የስኖዝለን ክፍል (Snoezelen room) ክፍል የብርሃን ተፅእኖዎችን ለመፍጠር ማይክሮፎን በመጠቀም እንደ ሙዚቃ ወይም በይነተገናኝ የድምፅ ማጉያ ጨዋታዎችን በመሳሰሉ ተግባራት ውስጥ በመሳተፍ የግንኙነት ክህሎቶችን ለማዳበር ይረዳል።

የመማር እና የባህሪ ችግሮች

ሴሬብራል ፓልሲ ያለባቸው ብዙ ልጆች እንደ ጠበኝነት ወይም ራስን መጉዳት ያሉ የመማር እና የጠባይ ችግሮች ሊኖራችህው ይችላል። የስኖዝለን ክፍል (Snoezelen room) ክፍል ሴሬብራል ፓልሲ እና ኦቲዝም ያለባቸውን ልጆች ባህሪ እንደ ሙዚቃ ማዳመጥ፣ መዝናኛ አካባቢን በማስመሰል፣ ወይም በይነተገናኝ መጫወቻ ሜዳ በመጠቀም ትኩረትን እና ማስተዋልን ለማሻሻል ይረዳል።

የ"አድቬንቸር ፕሌይ ግራውንድ ሩም" ለህፃናት ጀብደኛ ተግባራት የተነደፉ በርካታ ባለቀለም ቅርፆች እና እቃዎች የተገጠመለት ሰፊ ክፍል ነው። በመውጣት፣ መሰናክሎችን በማቋረጥ ወይም በኳስ ገንዳዎች በመጫወት በጡንቻ ማጠናከሪያ፣ ሚዛን ቁጥጥር እና የስሜት መነቃቃት ላይ ያተኩራል። እያንዳንዱ መሳሪያ ለልጆች ደህንነት ቅድሚያ ለመስጠት በጥንቃቄ የተነደፈ ነው።
በጨዋታ ላይ የተመሰረተ የሕክምና ቦታ በይነተገናኝ ፕሮጀክተሮች እና በይነተገናኝ የመጫወቻ ሜዳዎችን ከተለያዩ የስልጠና ጨዋታዎች ጋር ይጠቀማል። ጨዋታዎቹ የሚያተኩሩት አጠቃላይ የሞተር ክህሎቶችን በማሰልጠን፣ በተመጣጣኝ ቁጥጥር፣ በሞተር ቅንጅት ፣ ትኩረት እና ስሌት ላይ ነው።

የልጆችን አካላዊ ሕክምና ክፍለ ጊዜ ከትልቅ ስክሪን ቲቪ ለመመልከት የወላጅ መመልከቻ ቦታ

ቬጅታኒ ሆስፒታል ከፍተኛ ጥራት ያለው፣ ዘመናዊ፣ ደረጃውን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት የሚጥር ሲሆን ይህም የእድሜ ልክ ጤናን ለሁሉም እድሜዎች ለማሻሻል ነው። የነርቭ እና የእድገት ችግር ያለባቸው ልጆች በህፃናት ነርቭ ሳይንስ እና ማገገሚያ ማዕከል የባለሙያ እንክብካቤ እንደሚያገኙ እናረጋግጣለን።

Our Doctors

DR. TACHIPAT SEREEARUNO

Rehabilitation Medicine

Rehabilitation Medicine
DR. SUPACHAI LAOHAPONGSOMBOON

Pediatrics Neurology

Pediatrics
DR. CINDY CHAMROENNUSIT

Pediatrics Developmental and Behavioral

Pediatrics

ሌላ መረጃ

ጥቅሎች እና ቅናሾች

ተጨማሪ አሳይ

የታካሚ ታሪኮች

ተጨማሪ አሳይ

የጤና ጽሑፎች

ተጨማሪ አሳይ

የጤና ተንቀሳቃሽ ምስሎች (ቪዲዮዎች)

ተጨማሪ አሳይ