ቬጅታኒ ኪው ላይፍ (የሕይወት ጥራት) ማዕከል - Vejthani Hospital | JCI Accredited International Hospital in Bangkok, Thailand.

ቬጅታኒ ኪው ላይፍ (የሕይወት ጥራት) ማዕከል

በህይወትዎ ውስጥ በጣም አስፈላጊ እና ዋጋ ያለው ነገር ጤናዎ ነው። ወጣትነትዎን እና ደህንነትዎን ለመጠበቅ የጊዜ እና የፍላጎት ውድ ሀብት ማግኘት የህይወት መሰረታዊ ነገር ነው። በቬጅታኒ ኪው ላይፍ ከፍተኛ ልምድ ያላቸውን ፀረ-እርጅና እና ተሃድሶ ልዩ ባለሙያዎችን ከላቀ ሳይንሳዊ ፀረ-እርጅና ህክምና ጋር እናቀርባለን። በቬጅታኒ ኪው ላይፍ ላይ የሚገኘው ሆሊስቲክ ሜዲሲን የፈውስ አይነት ሲሆን ይህም የሰውን ሁሉ ጥሩ ጤንነት እና ደህንነት ፍላጎት ያገናዘበ ነው። የሕክምና ፕሮግራሞቹ የተነደፉት እንደ ዕድሜ፣ አንቲኦክሲዳንትስ (Antioxidants)፣ ጭንቀት፣ የቫይታሚንና ማዕድን እጥረት፣ ትክክለኛ ሚዛን እና ተስማሚ የአኗኗር ዘይቤን በመሳሰሉ ጉዳዮች ለእያንዳንዱ ግለሰብ ነው። የታካሚውን ልዩ ፍላጎቶች ለማሟላት እና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ለመጠበቅ ፣ የእርጅና ሂደቱን ለማዘግየት ፣ ከእድሜ መግፋት ጋር የተያያዙ በሽታዎችን ለመከላከል ወይም ለማዘግየት እና በመጨረሻም መልካም እና ሚዛናዊ ሕይወት ለማዳበር ለግል የተበጁ የመድኃኒት-ደረጃ ንጥረ-ምግቦች እና ሆርሞኖችን እናቀርባለን። የእኛ ቴክኖሎጂዎች ከእድሜ ጋር የተዛመዱ በሽታዎችን ለመለየት፣ ለመከላከል እና ለመቀልበስ ይረዱዎታል። ሂደቱን እንዲያልፉ እና አገልግሎቶቻችንን እንዲረዱ፣ ጤናዎን ለማሻሻል እና ወደነበረበት ለመመለስ በበሽታ መከላከል ላይ አስተያየት እና ምክሮችን ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች እንሰጣለን።
የተመረጠ ጥራት - በትኩረት የተሞላ እንክብካቤ ፀረ-እርጅና ሆሊስቲክ ሕክምና በቬጅታኒ ኪው ላይፍ የፈውስ አይነት ሲሆን ይህም የአንድን ሰው አጠቃላይ ገጽታ ግምት ውስጥ ያስገባ ነው። ጥሩ ጤንነት እና ደህንነትን ለማግኘት ባለው ዓላማ፣ የሕክምና መርሃ ግብሮች በሁሉም ረገድ የእያንዳንዱን ግለሰብ ፍላጎቶች ለማሟላት የተነደፉ ናቸው። ፕሮግራሞቻችን ከእድሜ ጋር ለተያያዙ በሽታዎች ህክምናን ፣አንቲኦክሲዳንት (Antioxidant) ማበልፀጊያ ፣ጭንቀትን መቆጣጠር ፣የቫይታሚን እና ማዕድን እጥረት ጉዳዮችን እንዲሁም የህይወት ሚዛንን እና ትክክለኛ የአኗኗር ዘይቤን ይሸፍናሉ። ታካሚውን በተናጥል ከገመገምን በኋላ የእኛ ልዩ ቡድን በመረጃ ላይ የተመሰረተ ምርመራ በመጠቀም የታካሚውን የግል ፍላጎት እና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ለመጠበቅ ፣የእርጅና ሂደትን ለማዘግየት ፣ከእድሜ ጋር የተያያዙ በሽታዎችን ለመከላከል ወይም ለማዘግየት ለግል የተበጁ የፋርማሲዩቲካል ንጥረ-ምግቦችን እና ሆርሞኖችን ለማዘጋጀት እንዲሁም በስተመጨረሻ ጥሩ እና ሚዛናዊ ሕይወትን ለማዳበር ይረዳል ።
ዝርዝሮች ለህይወት ጥራት ቁልፍ ናቸው ቬጅታኒ ኪው ላይፍ በ 11 ኛ ፎቅ ፣ ህንፃ A ፣ ቬጅታኒ ሆስፒታል ይገኛል። ማዕከሉ በሚያምር፣ ሰፊ፣ ሰላማዊ እና ስፓ በሚመስል አካባቢ ተዘጋጅቷል፤ ይህም የእርስዎን ግላዊነት የሚጠብቅ እና ዝግጁ መዳረሻ ያለው አገልግሎት ይሰጣል። ይህ ከጭንቀት ነጻ የሆነ ህክምናዎን ለማረጋገጥ ነው።

የአገልግሎት ሰዓታት

ሰኞ - አርብ : 08.00 am - 05.00 pm
ቅዳሜ - እሁድ : 08.00 am - 04.00 pm

ቦታ

ቬጅታኒ ኪው ላይፍ (የሕይወት ጥራት) ማዕከል፣ 11ኛ ፎቅ ፣ ቬጅታኒ ሆስፒታል

ቀጠሮዎች እና ጥያቄዎች

ይደውሉ: (+66)2-734-0000 Ext. 1125, 1126
የአማርኛ ስልክ መስመር: (+66)90-907-2560

አገልግሎቶች

  • ኪው ላይፍ ዌል ሆርሞን፡ የሆርሞን መጠን ምርመራ ፕሮግራም
  • ኪው ላይፍ የእድሜ መቆጣጠሪያ የማጣሪያ ምርመራ
  • መደበኛ የጤና ምርመራ የሆርሞን እና የቫይታሚን መጠን ምርመራ
  • የፀጉር መርገፍ የማጣሪያ ምርመራ
  • ኪው ላይፍ ተሃድሶ: አጠቃላይ የጤና ምርመራ የሆርሞን እና የቫይታሚን መጠን ምርመራ
  • የዘረመል ምርመራ
  • የማይክሮ ንጥረ ነገር፡ የቫይታሚን እና ማዕድን መጠን ምርመራ (16 ንጥረ ነገሮች)
  • በደም ስር የሚሰጥ የቫይታሚን መርፌ
  • ፒ.አር.ፒ (ፕሌትሌት-ሪች ፕላዝማ): ግሮውዝ ፋክተር (Growth Factor) መርፌ
  • በደም ስር የሚሰጥ የቫይታሚን ዲ መርፌ
  • ለግል የተበጀ ማሟያ ንጥረ ነገሮች
  • ሱፐር ሲ በደም ስር የሚሰጥ መርፌ
  • ቢ.ኤም.ዲ ዴክሳ (BMD DEXA) ቅኝት፡- የአጥንት ማዕድን እና የጡንቻ ምርመራ ከዱዋል-ኢነርጂ ኤክስሬይ አብዞርፕቲኦሜትሪ (Dual-Energy X-ray Absorptiometry) ጋር

Our Doctors

DR. ANJALY SRIMANOTHIP

Anti-Aging Medicine

Anti-Aging
DR. PRAEWPAILIN KUSOLMANOMAI

Anti-Aging Medicine

Anti-Aging
DR. THITI JESSADAROM

Anti-Aging Medicine

Anti-Aging

ሌላ መረጃ

ጥቅሎች እና ቅናሾች

ተጨማሪ አሳይ

የታካሚ ታሪኮች

ተጨማሪ አሳይ

የጤና ጽሑፎች

ተጨማሪ አሳይ

የጤና ተንቀሳቃሽ ምስሎች (ቪዲዮዎች)

ተጨማሪ አሳይ